የፍናን ፍቅረኛ እሺ ተብሏል
#ethiopia | ታዋቂዋ የፊልም ተዋናይት እና የማስታወቂያ ባለሙያ ፍናን ሕድሩ፣ ከረጅም ጊዜ የፍቅር አጋሯ ፍቅረአብ ከተባለ ወጣት ጋር ትዳር ለመመስረት በቀረበው ጥያቄ መሰረት፣ በዛሬው እለት በቤተሰቦቿ ዘንድ የሽምግልና ስነስርዓት ተካሂዷል።
በተዋናይቷ (በሴት ወገን) በኩል የቆሙት ሽማግሌዎች፣ በኮሜዲያን እና በማስታወቂያ ባለሙያው ዘላለም ኩራባቸው የተመሩ ሲሆን፣ በቡድኑ ውስጥ ታዋቂው የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁንም መካተቱ ታውቋል።
💍 "ጠንከር" ያለው የሽምግልና ሂደት
የወንዱ ወገን ሽማግሌዎች "ልጃችሁን ለልጃችን ስጡን" የሚለውን ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት፣ ከፍናን ቤተሰቦች እሺታን ከማግኘታቸው በፊት፣ በዘላለም ኩራባቸው እና በሰይፉ ፋንታሁን በኩል ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች ቀርቦ እንደነበር ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
ምንጮች እንደገለጹት፣ "የፍናን እጮኛ ከዚህ በፊት ህይወት የለውም ወይ?" (የቀድሞ የትዳር ታሪክ) የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተው ነበር። ይህ ባልተጠበቀ ጥያቄም የወንዱ ወገን ሽማግሌዎች "እሺታን ላናገኝ እንችላለን" በሚል ስጋት ውስጥ ገብተው እንደነበር ተገልጿል።
በጥያቄዎቹ መሰረት፣ በዘላለም ኩራባቸው የሚመሩት የሴት ወገን ሽማግሌዎች "አንዴ ውጪ ቆዩንና እንመካከርበት" በማለት የወንዱን ወገን ሽማግሌዎች ከቤት አስወጥተው ለደቂቃዎች እንዲቆዩ አድርገዋል።
💍 የመጨረሻው ምላሽ
ከምክክር በኋላ ወደ ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉት ሽማግሌዎች፣ ምላሹን በጉጉት ሲጠባበቁ በኮሜዲያን ዘላለም ኩራባቸው በኩል የሚከተለው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፦
"የማይመታት፣ የማይፈታት ሚስቱ ትሁን ብለን ፈቅደናል!"
ይህንን ምላሽ የሰሙት እና በከፍተኛ ስጋት ውስጥ የነበሩት የወንድ ወገን ሽማግሌዎች፣ በደስታ እሺታውን መቀበላቸውን በስፍራው የነበሩ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
💍 ስለ ፍናን ሕድሩ አጭር መረጃ
ውልደቷና እድገቷ በአዲስ አበባ የሆነው ፍናን ሕድሩ፣ በለጋ እድሜዋ ከህዝብ ጋር የተዋወቀችው በድምጻዊ እሱባለው ይታየው "ማሬ ማሬ" በተሰኘው የሙዚቃ ክሊፕ ላይ በመታየት ነው።
ይህን ተከትሎም ወደ ፊልም ትወና በመግባት "ቦሌ ማነቂያ" እና "የከበረ ደሃ" በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት በመስራት ዝናዋን አሳድጋለች።
ፍናን ከትወናው ባሻገር በማህበራዊ ሚዲያ ስራዎቿ ትታወቃለች። በኢንስታግራም ከ1 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሏት ሲሆን፣ ለተለያዩ የንግድ ተቋማት በማስታወቂያ ስራ ከፍተኛ ተከፋይ ከሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች አንዷ ናት። ፍናን ለመጀመሪያ የማስታወቂያ ስራ 600 ብር እንደተከፈላት የምትገልጽ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለአንድ ማስታወቂያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተከፋይ መሆኗን ትናገራለች ያለው ዘሃበሻ ነው።

9 months ago