Logo
Getu Temesgen
''እኔ ከመጣሁ ወዲህ እኔ እንኳን የማውቀው የአራት የኢትዮጵያውያንን አስክሬን ሸኝተናል'' ዘማሪ መስፍን ጉቱ
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ 2 ኢትዮጵያዊያን ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ፡፡ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከዚህ ቀደም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በኢትዮጵያዊያን ላይ ግድያ መፈፀማቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም ይህ ድርጊት መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡

በትላንትናው እለትም መላኩና አክሊሉ የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በደርባን ከተማ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡ የእነዚህ ወጣቶች የአስከሬን ሽኝት በዛሬው እለት በደርባን ዌስት ስትሪት ቤተክርስቲያን ተከናውኗል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ2 ቀናት በፊት ደግሞ በጆሀንስበርግ ነዋሪ የነበረው ሚካኤል አበበ ከስራ ወደቤቱ በሚመለስበት ወቅት በበርካታ ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል፡፡

የ3 ልጆች አባት የሆነው ሚካኤል አስከሬን ሽኝትም በትላንትናው እለት በጆሀንስበርግ ኬብሮን ቤተክርስቲያን ተከናውኗል፡፡ በትላንትናው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ላይ ከተገኙት መካከል ታዋቂው ዘማሪ መስፍን ጉቱ የሚገኝበት ሲሆን በወቅቱ ሲናገርም ‹‹እኔ ጆሀንስበርግ ከተማ ከመጣሁ በአንድ ወር ከሁለት ሳምንት ሆኖኛል፡፡ ይሄ ነገር ለእኔ እንግዳ ሆኖ እንደሆነ ባላውቅም የተለመደ ሆኖብኛል፡፡ እኔ ከመጣሁ ወዲህ እኔ እንኳን የማውቀው የአራት የኢትዮጵያዊያንን አስሬን ሸኝተናል፡፡ እግዚአብሄር በቃ ሊለን ይገባል›› ብሏል፡፡

ጨምሮም ‹‹ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? በቃ ብለን አሁኑኑ መፀለይ ይገባናል፡፡ እጃችንን አንስተን እግዚአብሄር እንዲምረን እንፀልይ›› በማለት ሲናገር ተመልክተናል ያለው ዘሃበሻ ነው፡፡

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.