Logo
YenetaTube
እኔ የተወለድኩበት አካባቢ ያደገ አማርኛዉ ደስ የሚል የገጠሩን ለዛ የተላበሰ አንድ ወጣት ባለሀብት
ጎበዝ ነጋዴ በሰዎች በኩል አስተዋወቁኝ ብሎ ተዋወቀኝ።

ምንያህል ስራዎቼን እንደሚያደንቅና እንሚወደኝ ነግሮኝ የጋብቻ ጥያቄ አቀረበልኝ እኔም ስለ ቀና አመለካከቱ አመስግኜ በጌታ ነህ ወይ ብዬ ስጠይቀዉ አይ ጌታን አልተቀበልኩም አንቺ ጥያቄየን ከተቀበልሽ ጌታን እቀበልልሻለሁ አለኝ🙄
ልጁ ፍፁም የዋህና ቀጥተኛ ሰዉ ነዉ።

እኔም ለኔ ብለህ ሳይሆን ለራስህ ብለህ ተቀበል ብዬ ጌታን የመቀበል ጥቅማ ጥቅሞቹን አስረዳሁ።ከዚያም አንድ የምወደዉ አገልጋይ ጠርቼ እሱ እንዲፀልይለት አደረኩ።

በነጋታዉ ይሄዉ ነጋዴ ደዉሎ ፣እህሳ አለኝ ጌታን ተቀበልኩ በይ አሁን ፍቅራችንን እንጀምር ሲለኝ አሁን መሰረታዊ የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት ተማር ከዚያ በሗላ ነዉ ደግሞ የጌታ ፈቃድ መሆኑን መወያየትም መፀለይም የሚቻለዉ አሁን ስለምንም ጎዳይ ማዉራት አይፈቀድም ስለዉ
ኧሯ እና ከተማርሁ በሗል እንጃልህ ብትይኝስ ሲለኝ እና በመማርህ የዘለአለም ህይወት አትርፈህ መሄድ ነዉ ምንም አትጎዳም ስለዉ ብዙም አልተዋጠለትም።

ከተወሰነ ቀናት በሗላ የመኪና መሸጫ ቤት ሄዶ ደወለልኛና ነይ አሁኑኑ የ6 ሚሊየን ብር መኪና በስምሽ ገዝቼ ልስጥሽ አለኝ ፣ የምሩን እኔን ለማስደሰትና ለማሳመን አስቦ ነበር።

እኔም ቆጣ ብዬ ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ? ይሄ ለኔ ስደብ ነዉ ስለዉ ብስጭት ብሎ ኧረ ይድፋሽ ምኒቱ ናት አያ አለ፣ አዎ ንቀት ነዉ ስለዉ ኧረ እልም ያርግሽ አለኝ።

እንደዚህ ማለቱ በጣም አሳቀኝ፣ ቆጣ ብሎ እኔ ላንቺ ካለኝ ትልቅ አክብሮት እንጅ
ለማንም ልጃገረድ እንኳ ፈፅሞ የማላደርገዉን ነዉ ላንቺ አስቤ ልግዛልሽ ያልኩሽ ሲለኝ የኔ ዋጋኮ ከልጃገረድ ዋጋ እጅግ ይበልጣል ስለዉ እየሳቀ ተይ እንጅ የሁለት ልጆች እናት መሆንሽን አትርሺ እኔ ስላከበርኩሽ ነዉ ልግዛልሽ ያልኩሽ ሲለኝ ፣እኔም በገንዘብ ልታሳምነኝ መሞከርህ ከክብሬ አዉርዶ የሚፈጠፍጠኝ እንጂ የሚያከብረኝ አይደለም አርፈህ የእግዚአብሔርን ቃል ተማር ብዬ ዘጋሁበትና የሩቅ ወዳጆች ሆነን ቀረን።

ወንዶች ሁሉ ራሳችሁን ለፍቅር ወይም ለትዳር ብቁ ለማድረግ ቀዳሚዉ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ!
በትዳር ዉስጥ ገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነዉ
ነገር ግን ዋና ነገር አይደለም ዋናዉ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ!

Sofia shebabaw

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.