ከሚስቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የ9ወር ልጁን የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
#ethiopia | በቢሾፍቱ ከተማ ዲባዩ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነው እሸቱ ነገሰ ቢሾፍቱ ከተማ ቢፍቱ የተባለ አካባቢ ከአንዲት ወጣት ጋር በመተዋወቅ ትዳር መስርተዋል፡፡እሸቱ እና ባለቤቱ በትዳር ለተወሰነ ጊዚያት ከቆዩ በኋላ ትዳራቸው በጥርጣሬ እና በቅናት አለመግባባት ይፈጠር እንደነበረ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አቃቢ ህግ ፅ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ቡድን መሪ አቃቢ ህግ ሰኚ ነሙምሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሁለቱ ጥንዶች መካከል በቅናት የተነሳ አለመግባባቶች ቢኖሩም ሚስት አርግዛ ወንድ ልጅ ትወልዳለች። ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ግጭታቸው የተረጋጋ ቢመስልም እሸቱ ከውጭ በሚሰማው ተጨባጭ ያልሆነ ወሬ በመካከል የተረጋጋው ትዳር ተመልሶ በቅናት ስሜት ወደ ግጭት ማምራቱ ነው የተገለፀው።ይሁን እንጂ በድጋሚ በተፈጠረ አለመግባባት ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በባል እና ሚስት መካከል ግጭት ተፈጥሮ ሚስት የዘጠኝ ወር ህፃን የሆነውን ጉዲና እሸቱን ይዛ ከቤት ትወጣለች። በዚህ ግዜ ባል እሸቱ ነገሰ ሚስትን ተከትሎ ወደ ቤት ተመለሺ የሚል ትዕዛዝ በመስጠት ሲጨቃጨቁ የአካባቢ ጎረቤት ሰምተው ሲያገላግሉ ልጄን አምጪ በማለት የዘጠኝ ወሩን ህፃን ልጅ ከእናቱ እቅፍ ነጥቆ ወደ ቤት ይገባል።
በዚህ ግዜ እናት ልጄን ተቀበሉልኝ እያለች ስትጮህ የጎረቤት ሰው አይዞሽ ለሱም ልጁ ነው ምንም አያደርገውም ብለው አረጋግተው ይይዟታል።የአካባቢው ሰው በዚህ መልክ ነገሮችን ካረጋጉ በኋላ ጥቂት ቆይተው ባለቤቷ አነጋግረው ለማስታረቅ ወደ መኖርያው ቤት ሲገቡ የዘጠኝ ወር ልጁን ከእናቱ ነጥቆ ስለት ባለው ብረት አንገቱን በመምታት መግደሉ ተገልጿል ።የድርጊቱ ፈጻሚ እሸቱ ነጋሳ በጨቅላው ህፃን ላይ ድርጊቱን የፈጸመበት ምክንያት ያልተጨበጠ ወሬ እና ቅናት እንደሆነ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውል በሰጠው ቃል አረጋግጠዋል ሲሉ አቃቢ ህግ ሰኚ ነሞምሳ ገልፀዋ።
ፖሊስ የምርመራ መዝገቡ በህጻኑ የአስክሬን የምርመራ መዝገብ እና በወቅቱ በነበሩ ሰዎች በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ልኳል፡፡ አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ ቁጥር 539 በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል።በአቃቢ ህግ የተከፈተውን የክስ መዝገብ የተመለከተው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድቤት ጥቅምት 10 ቀን 2018ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ እሸቱ ነገሰ በምንም መንገድ ከሰው ልጅ በማይመነጭ ጭካኔ እና ነውረኛ በሆነ መልኩ እራሱን መከላከል የማይችል ጨቅላ ልጁን መግደሉ አደገኛነቱን የሚያሳይ በመሆኑ በ22 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ያለው ብስራት ኤፍ ኤም ነው ።

9 months ago