በሳምንት ደሞዝ ሳይቀነስ የአራት ቀን ብቻ ስራ ውጤታማ ሆነ
📌ማይክሮሶፍት ጃፓን የአራት ቀን የስራ ሳምንትን ስትሞክር የሰራተኞች ምርታማነት በ40% ጨመረ
#ethiopia | የቴክኖሎጂ ግዙፉ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ጃፓን በ2019 ዓ.ም ያካሄደችው ደፋር ሙከራ አስገራሚ ውጤት አስመዝግቧል።
ኩባንያው ለሠራተኞቹ ደመወዝ ሳይቀንስ በሳምንት ለአራት ቀናት ብቻ እንዲሠሩ፣ አርብ ቀንን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እረፍት የሚሰጥበትን መርሃ ግብር ዘርግቶ ነበር።
ሙከራው "Work-Life Choice Challenge Summer 2019" በሚል ስም የተካሄደ ሲሆን፣ ውጤቶቹም የሥራ አቅምንና ቅልጥፍናን በተመለከተ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል ተብሏል።
ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የሠራተኞች ምርታማነት (በሠራተኛ የሚመነጨው ሽያጭ) 40% ከፍ ብሏል ነው የተባለው።
የኤሌክትሪክ ፍጆታ መጠን በ23% የቀነሰ ሲሆን፣ የታተመው የወረቀት መጠን ደግሞ 60% ያህል ቀንሷል። ይህም የአካባቢ ጥበቃ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ያሳያል።
ከሠራተኞቹ ውስጥ 92% የሚሆኑት በአራት ቀናት የሥራ ሳምንት መርሃ ግብር መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ማይክሮሶፍት ጃፓን ምርታማነቱ መጨመር በዋናነት የመጣው በሥራ ላይ ባለው ቅልጥፍና ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል።
ስብሰባዎች አጭር እንዲሆኑ (ቢበዛ 30 ደቂቃ) እና ዓላማቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ተደርገዋል።
ሠራተኞች የሶስት ቀን እረፍት ማግኘታቸው ተመልሰው ሲመጡ በትኩረትና በሙሉ ጉልበት እንዲሰሩ አግዟቸዋል።
እንደ መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ በአጠቃላይ፣ ይህ ሙከራ በሠራተኞች የግል ሕይወት እና በሥራ መካከል ጥሩ ሚዛን ሲፈጠር፣ ውጤታማነት እንደሚጨምር በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው ተብሏል።

8 months ago