Logo
YenetaTube
የቅዱስ ያሬድ ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

አንዲት ትል ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ስትወጣና ስትወርድ ከቆየች በኃላ በሰባተኛው ዛፉ ላይ ወጥታ የዛፉን ፍሬ ስትበላ ተመልክቶ በወሰደው ትምህርት ትሏ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበችውን ስታሳካ ራሱን በመውቀስ ወደ መምህሩ ተመልሶና ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን እንደቀጠለ በሚነገረው አስደናቂ ታሪኩ በርካቶች ያውቁታል፡፡

ሚያዝያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይሥሐቅ እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ይባላሉ። በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ የነበረው አጎቱ ጌዴዎን እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለሰባት ዓመት ተምሮ ፈቀቅ ባለማለቱ አንድ ቀን አጎቱ ተቆጥቶ ገርፈው፡፡ መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ሄዶ ተደበቀ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በዛፍ ስር አርፎ እያለ የያችን ትል ትግል ተመለከተ፡፡

ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ በመሔድም ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በጣም በአጭር ጊዜም 150 መዝሙረ ዳዊት፣ መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችንና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ ዜማ ባልነበረበት በዚያ ዘመን በስልት እያነበቡ ያመሰግኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ኅዳር 5 ቀን 527 ዓ.ም በኤዶም ገነት በሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ፤ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝልና በአራራይ ዜማ ማዜምን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ገልጹለት፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጎም “ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን….” ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው” ማለት ነው፡፡

በ534 ዓ.ም ኅዳር 6 ቀን ወደ ሰማይ ተነጠቀ፤ በሰማይ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ልዩ በሆነ ጣዕመ ዝማሬ ሲያመሰግኑ ሰማ፡፡ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ አክሱም ጽዮን ውስጥ ወደ ምሥራቅ በኩል በመዞር ከሰማይ የሰማውን ዝማሬ ዘመረ፤ አርያም ብሎም ሰየመው፡፡ በዚሁም በ538 ዓ.ም ቅዱስ ያሬድ ማኅሌት ጀመረ፡፡ አሁን ድረስ የሚያገለግሉ ድጓ፣ ጾመድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕትና ምዕራፍ የሚባሉ አምስት የዜማ መጻሕፍትም ደርሷል፡፡ ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” ይባላል፡፡ ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡

ይህን ዜማ ከፍ አድርጎ ሲያዜም ሰው፣ እንስሳትና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ልዩውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የግእዝ ብሎም የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራችም ነው፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ ከሊቃዉንት እያጣቀሰ መንፈሳዊ ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በመጨረሻ በተወለደ በ75 ዓመቱ በገዳማዊ ሕይወት በኖረበት በሰሜን ተራሮች ደብረ ሐዊ ገዳም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡

ገዳማውያን እንኳን ዓለማዊ ደስታ ሊመኙ መንፈሳዊ ክብራቸውም በሰው ፊት እንዲገለጽ አይሹም፡፡ ለኛ ለደካሞቹ ግን ሁሌም ይጸልዩናል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.