Logo
FIDEL POST NEWS
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች በሬሚዲያል መርሀ-ግብር ተማሪዎች እንደማይቀበሉ ተነገረ

ሚኒስቴሩ በ2017 ዓ.ም የ12 ክፍል ፈተና ተፈትነው በሬሚዲያል መርሀ-ግብር የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን የሚያስተካክሉበት ቀንን ይፋ አድርጓል፡፡

በእዚህ መሰረት ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ( https://student.ethernet.e... ) በመግባት ማስተካከል እንደሚችሉ ተናግሯል፡፡

የተቋም ምርጫ የሚደረገውም በየትምህርት ቤቶች በተወከሉ መምህራን በኩልም ነውም ብሏል፡፡በሀገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥም ሰባቱ በሬሚዲያል መርሀ-ግብር ተማሪዎች እንደማይቀበሉም ተነግሯል፡፡

ተማሪዎች አይቀበሉም የተባሉት፤ ሀዋሳ የኒቨርሲቲ፣ ጅማ የኒቨርሲቲ፣ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ናቸው ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገፁ ባጋራው መረጃ።

Via ShegerMinistry of Education PortalStudent Admission and Placement Portal
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.