ደፋሮቹ የጦርነት ዘጋቢዎች ተሸለሙ !
በድፍረት በሙያዊ መታመን በእሳት ውስጥ ደፍረው በመግባት ጋዛ፣ ሶሪያ፣ ዩክሬን ኢትዮጵያ የተከሰቱ ግጭቶችና ጦርነቶች ለአለም ያሳወቁ የጦርነት ዘጋቢዎች ዓመታዊው የBayeux ሽልማት ማግኘታቸው ተነገረ ።
በትላንትናው እለት የፈረንሳዩዋ የባዩ ከተማ በተካሄደው የጋዜጠኞች የጦርነት ዘጋቢ የሽልማት ስነ ስርዓት ለ32ኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን፤ ፍልስጤማዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሳሄር አልግሆራ፣አሊ ጀዳላህ (አናዶሉ ኤጀንሲ)፣ ጄሃድ አልሽራፊ፣ ቮልፍጋንግ ባወር (ዘይት ማጋዚን) የስዊዘርላንድ-ካናዳዊ ጋዜጠኛ ሞሪን ሜርሲየር እንዲሁም ስለኢትዮጵያ ዶክመንተሪ ፊልም የሰራችው ማሪያኔ ጌቲ (ክራከን ፊልምስ/አርቴ) ጨምሮ በርካታ ዘጋቢዎች ተሸልመዋል ።
ለዙማ ፕሬስ የሚዘግበው ፍልስጥኤማዊ የፎቶ ጋዜጠኛ ሳሄር አልግሆራ ለሁለት ዓመት ገደማ በጋዛ ሰርጥ በሃማስና እስራኤል መካከል ሲካሄድ የቆየውን አውዳሚ ጦርነትና የደረሰውን አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ «በእሳት እና ረሃም መካከል » በተሰኘውና በተከታታይ በሰራቸው የፎቶ ዘገባዎች በመስራቱ ለሽልማት መብቃቱ እንዲሁም ከሳሄር በተጨማሪ የጀርመኑ የሳይት ጋዜጣ ዘጋቢ ዎልፍ ጋንግ ባየር፣ በህትመት ጋዜጠኝነት ዘርፍ አሸናፊ መሆኑ ተነግሯል።
በሕትመት ጋዜጠኝነት ዘርፍ ቮልፍጋንግ ባወር (ዘይት ማጋዚን) በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም አሁንም ቀዶ ጥገና በማድረግ ተግድሎ እየፈፀመ የሚገኝ ሆስፒታል “የተረሳው” በሚል በሰራው ስራ አንደኛ በመሆን አሸንፏል።
ጋዜጠኛው በእንባ ታጅቦ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት በሆስፒታሉ የሚገኙትን "ዶክተሮች፣ ነርሶች እና በጎ ፈቃደኞች በየቀኑ የሚቻለውን ሁሉ ለሚያደርጉ በሙሉ" ምስጋና አቅርቧል።
በቴሌቭዥን ዘርፍ ጁሊ ደንገልሆፍ፣ ጀምስ አንድሬ እና ሶፊያ አማራ ከፈረንሳይ 24 አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል፣ “ውስጥ የአሳድ የሽብር ማሽን” በሚል ዘገባ በሶሪያ መንግስት ነፃ ባወጣቸው እስር ቤቶች ላይ ያተኮረ ስራቸዉ ለዚህ ክብር አብቅቷቸዋል ።
በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት “ትግራይ፡ መደፈር፣ ዝምተኛው መሳሪያ” የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም የሰራች ማሪያኔ ጌቲ (ክራከን ፊልምስ/አርቴ) በኬን መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው ሽልማቴ ግራንድ ፎርማት የቴሌቭዥን ዋንጫ አሸንፋለች ።
ከሲኤንኤን ዘጋቢዎች ጆማና ካራድሼህ፣ ታረቅ አል ሂሉ፣ መሀመድ አል ሳዋሊ፣ ሚክ ክሬቨር እና ማርክ ባሮን ስለ ጋዛ ህፃናት ህይወት በሰሩት ዘጋቢ ፊልም በተማሪዎች እና በሰልጣኞች የተሰየመውን ልዩ የኖርማንዲ ሪጅን ሽልማት አግኝቷል።
በአሜሪካዊው ጋዜጠኛ ጆን ሊ አንደርሰን የሚመራው የBayeux Calvados-Normandy Award ለ32ኛ ጊዜ ባዘጋጀው ሽልማት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ ዳኞች ድምፅ መሰረት በማድረግ በአስሩ ምድቦች አሸናፊዎችን እንደመረጡ ተናግረዋል ።
አሸናፊዎች በጣም ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሙያ የገባቸው መሆኑን በመግለፅ አክብሮታቸዉን ገልፀዋል ።
በስነ ስርዓቱ ላይም በቅርቡ በስራ ላይ እያሉ ለተገደሉ ጋዜጠኞች ክብር ተሰጥቷል ሲል ያስነበበው France 24 ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago