Logo
Getu Temesgen
ፍልስጤማውያን ወደ ጋዛ እየተመለሱ ነው
#ethiopia | በጋዛ የተኩስ አቁም ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ መመለስ ጀምረዋል፡፡

የእስራዔል ጦር የትራምፕ የሰላም ዕቅድ ስምምነትን ተከትሎ በጋዛ የተኩስ አቁም መተግበር መጀመሩን አስታውቋል።

የእስራዔል ካቢኔም የሰላም ዕቅዱን ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ማፅቀዱ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የእስራዔል ጦር ከጋዛ በመውጣት ወደ ተስማሙበት መስመር ወጥቷል።

በቀጣይ ሁለቱ አካላት የእስረኞች ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን፥ በርካታ መጠን ያለው ሰብአዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ ይገባል።
#arada

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.