Logo
SeledaPost
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው ኢትየሃድ ወደ አዲስ አበባ እለታዊ በረራ ጀመረ።

በማብሰሪያ በረራው የኢትሃድ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ ከፍተኛ ሃላፊዎችን የያዘ አውሮፕላን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ከፍተኛ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በወቅቱ የኢትሃድ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶኖአልዶ ኔቬስከ፣አየር መንገዳቸው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከበርካታ አየር መንገዶች ጋር እንደሚሰራ ያስታወሱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ ከኢትሃድ ጋር ያለን ትብብር ግን የተለየ ነው ሲሉ ነው በበረራ ማስጀመሪያው ወቅት መናገራቸውን ካፒታል ዘግቧል፡፡

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.