ለፍትህና ሰብአዊነት በመታገላችን በእስራኤል ተበድለናል ! ደቡብ አፍሪካውያን /
እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመች ነው የሚለውን ውንጀላ በፅኑ ውድቅ ያደረገች ሲሆን ደቡብ አፍሪካን ጉዳዩን በማቅረብ የሃማስ "ህጋዊ ክንድ" ነች ስትል ከሰሰች።
በእስራኤል እስር ከተዳረጉ ወደ ጋዛ ሰብአዊ ድጋፎችን ለማድረስ ከተጓዘዉ የግሎባል ሱሙድ ፍሎቲላ የበጎ አድራጎት ቡድን አካል የሆነው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት እና የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ በእስራኤል ለቀናት ከታሰሩና ከተባረሩ በኋላ ረቡዕ እለት ጆሃንስበርግ መግባታቸው ተሰማ ።
ከሌሎች አራት ደቡብ አፍሪካውያን ጋር ወደ አገራቸው የተመለሱት ማንድላ ማንዴላ፣ እሱና አብረውት የነበሩት ቡድን በእስራኤል እስር ቤት ለስድስት ቀናት ታስረው በዮርዳኖስ በኩል መለቀቃቸውን ተናግረዋል።
ደቡብ አፍሪካ እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅማለች በሚል መክሰሷን ተከትሎ በፍሎቲላ ላይ ከነበሩ በተለየ የደቡብ አፍሪካ አክቲቪስቶች “አስቸጋሪ ሁኔታ ደርሶባቸዋል” ብለዋል ።
አያያዛቸውን በተመለከተም "ምክንያቱም እኛ አፓርታይድ እስራኤልን ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እና አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወስደን ተጠያቂ ለማድረግ በመንግስታችን በኩል የደፈርን ህዝቦች ነን" ብለዋል ማንድላ ማንዴላ።
የደቡብ አፍሪካ አክቲቪስቶች መካከል የሆነች ፋጢማ ሄንድሪክስ እና ዛሂራ ሱማር ወደ ጆሃንስበርግ OR ታምቦ አየር ማረፊያ ከተመለሱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በእስራኤል ተይዘው በግዳጅ ሂጃብ ከጭንቅላታቸው ላይ መውጣቱን እና ይህም ከደቡብ አፍሪካውያን ዉጭ በሌሎች ሙስሊም ሴት አክቲቪስቶች ላይ አልደረሰም። ብላለች ።
ሱማር "ሁለታችንም ደብብ አፍሪካውያን በተለየ መልኩ ተንገላተናል፣ ጭንቅላታችን ግድግዳው ላይ ተገፍቶ በእስራኤል ወታደሮች ፊት ራቁታችንን አውልቀን እንድንቆም ተደርጎ ነበር። ይህ በሌሎች ሴቶች ላይ አልደረሰም።" ፓስፖርታችንን በማየት እኛ እንደ ደቡብ አፍሪካውያን መሆናችንን ካወቁ በኋላ ለመናገር የሚከብድ ክብረነክ ተግባር ፈፅመዉብናል ።ብላለች
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንም አይነት እንግልት ተፈጽሞብኛል ያለውን የይገባኛል ጥያቄ በጽኑ አስተባብሏል፣ ሁሉም የመብት ተሟጋቾች ያለ እስር በገዛ ፈቃዳቸው እንዲባረሩ እድል እንደተሰጣቸውም ጠቁሟል። ሲሉ የዘገቡት ሮይተርስ ጀሩሳሌም ፖስት ኒዮርክ ታይምስ ናቸዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago