Logo
Getu Temesgen
የእርዳታ ተማጽኖ
#ethiopia | ወንድማችን ዮሐንስ ይባላል። ዮሐንስ አበበ። ትውልድ እና እድገቱ በዉቢቷ የስኳር ከተማ ወንጂ ሲሆን ኑሮውን ደግሞ በፍቅር ከተማዋ በአዋሳ ካደረገ ረጅም አመታት ተቆጥረዋል።

ዮሐንስ /ወዳጆቹ እንደሚጠሩት ጆን/ በልጅነቱ ባጋጠመው አደጋ አካል ጉዳተኛ ቢሆንም በተለያየ የእጅ ሙያ በአዋሳ ከተማ እየሰራ እና እየኖረ ነበር።

በ2017 ዓ.ም የደረሰበት ድንገተኛ የመኪና ግጭት አደጋ ግን ተጨማሪ የአካል ብሎም የስነልቦና ጉዳት አስከተለበት። ኦፕራሲዮን በማድረግ ብረት ገብቶለት እያገገመ ባለበት ሁኔታ የኒሞኒያ በሽታ ይዞት በጣም ታመመ።

እንደሚታወቀውም መድሃኒቱ ከባድ እና ለረጅም ጊዜ የሚወሰድ በመሆኑ የጎንዮሽ ጉዳት ይዞበት መጣ። እናት እና አባታችን በህይወት የሌሉና አዋሳ የምትኖር እህታችን በቅርብ ያለችው እሷ በመሆኗ ስታስታምመው ቆይታ ስለባሰበት እና ከእሷም አቅም በላይ በመሆኑ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በሌላኛዋ እህታችን አማካኝነት ህክምናውን እዚሁ ቀጠለ።

በግል ህክምና ተቋማት የተለያዩ ምርመራዎች እና ህክምናዎች ቢያደርግም ሊሻለው ስላልቻለ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ቢደረግለትም ሁለቱም ኩላሊቶቹ መስራት የማይችሉበት ደረጃ በመድረሳቸው ከሶስት ወር በላይ ተኝቶ ሲታከም ቆይቶ የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድርገው በነበረ ጊዜ እጅግ በጣም በመታመሙ እና ዳያለስስ በአስቸኳይ ይጀምር በመባሉ ከሆስፒታል ወጥቶ በግል የዳያለሲስ ህክምናውን ለማድረግ ተገደድን። ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ዳያለሲስ እያደረገ ቢቆይም ህመም እና ስቃዩ እየጨመረ እንጂ ለውጥ አልታየበትም።

ዮሐንስ ከሆስፒታል ደጅ ሳይርቅ ወደዚህም አመት የተሻገረ እና በአሁኑ ሰዓት በጳውሎስ ሆስፒታል ተኝቶ በህክምና እየተረዳ ይገኛል። ባለው ወረፋ እና የማሽን እጥረት ምክንያት ወደ ውጪ እየወጣ በግል ዳያለሲስ እያደረገ ተመልሶ የሚገባ ሲሆን የዳያለሲስ ህክምና ወጪውም በአሁን ሰዓት ከእኛ አቅም በላይ ሆኖ በየቀኑ ማድረግ የነበረበትን ዳያለስስ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያደረገ እርሱም ህመሙ እየባሰበት እና እየተሰቃየ ይገኛል።

በነዚህ ከባድ ጊዜያት ከእኛ ጋር የነበረ እና አሁንም ያለውን እግዚአብሔርን ቀጥሎም ከጎናችን የነበራችሁትን የወንጂ የአዋሳ እንዲሁም የናዝሬት ልጆች የቤተሰባችን ወዳጆች በቅርብም በሩቅም ያላችሁትን እያመሰገንን መላው አዛኝ እና ደጋግ ኢትዮጲያዊያን እና ኤርትራዊያን በአገር ውስጥ ከአገር ውጪም ያላችሁ በሙሉ ወንድማችን ዮሐንስን ለማሳከም በምትችሉት ሁሉ ቀኝ እጃችሁን እንድትሰጡን እንድታግዙን እና እንድትደግፉን
በታላቅ አክብሮት እየጠየቅን ስለምታሳዩን ትብብር ምስጋናችንን ከወዲሁ እናቀርባለን ውለታችሁን እግዚአብሔር ይክፈል ፀሎታችሁ አይለየን ።

እህቶቹና ወንድሞቹ
ገነት አበበ ግርማ አበበ
ክብ ነሽ አበበ ጉልላት አበበ
ሣምራዊት አበበ

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
ክብነሽ አበበ 1000073875858
ሳምራዊት አበበ 1000154010908

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.