ፑቲን ባቀረበው ሃሳብ እስማማለሁ ! /ትራምፕ /
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያቀረቡትን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማምረትና መታጠቅ ገደብን የሚጥለው የ"አዲስ START ስምምነት" ለተጨማሪ አንድ አመት የማራዘም ሀሳብ በደስታ መቀበላቸው ተነገረ ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ በዋይት ሀውስ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደተናገሩት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአዲሱ START ስምምነት ለመቀጠል ሀሳብ ማቅረባቸዉ ጥሩ መሆኑን በመግለፅ ዋሽንግተንም ትቀበለዋለች ብለዋል ።
ይህ የዋሽንግተን ምላሽ የተሰማው እሁድ እለት ፑቲን የሁለቱ ስምምነት በየካቲት ወር ካለቀ በኋላ ሩሲያ የስምምነቱን የቁጥር ገደቦችን ለተጨማሪ አንድ አመት መከተሏን ለመቀጠል መዘጋጀቷን መግለፃቸውንና ይህ እርምጃ ተግባራዊ የሚሆነው ዋሽንግተን ይህን ከተከተለ ብቻ እንደሆነ አጽንኦት መስጠታቸው ተከትሎ ነዉ ።
ትራምፕ በዋይትሐውስ ስለ ሃሳቡ ሲጠየቁ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ለእኔ ጥሩ ሀሳብ ይመስላል" ብለዋል ።
ትራምፕ" የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአዲሱ የስትራቴጂክ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት ላይ የተቀመጡትን ገደቦች ለማክበር ያቀረቡት ሀሳብ 'ጥሩ ሀሳብ ይመስላል' ከዩክሬን ጋር ስላለዉ ሁኔታም የተደረገው ውይይት ውስብስብ ቢሆንም መፍትሔ አናጣም ብለዋል።
ዋሽንግተን ፈጣን ምላሽ መስጠቷን ሞስኮ በበጎ እንደተመለከተችዉ የገለፁት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "በእርግጥ እንዲህ ያለውን መግለጫ በደስታ እንቀበላለን። "ይህ ቀደም ሲል ዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዚዳንት ፑቲንን ተነሳሽነት ትደግፋለች የሚል ብሩህ ተስፋን ይሰጣል ብለን እናምናለን." ብለዋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጋዜጠኞች ለትራምፕ " ፑቲን ዩናይትድ ስቴትስ የቶማሃውክ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ብታቀርብ አደገኛ አዲስ ፍጥጫ እንደሚፈጥር ማስጠንቀቃቸውን በተመለከተ ጥያቄ ቢቀርብላቸው ምላሽ ለመስጠት አልፈለጉም ።
እንደሚታወሰው ስለ ሰላም ስምምነቱ ከአሁን በፊት ሞስኮ አቋሟን በተደጋጋሚ ያሳወቀች ሲሆን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ቅዳሜ እንደተናገሩት ሞስኮ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም ለድርድር ክፍት ነው, የሩሲያ የደህንነት ስጋቶች እና የሩስያ ቋንቋ ተናጋሪዎች መብቶች ከማንኛውም እልባት በፊት መቅረብ አለባቸው. ብለዋል ።
አክለው "ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደጋግመው አጽንኦት ሰጥተው እንደገለፁት ሩሲያ የግጭቱን መንስኤዎች ለማስወገድ ለድርድር ክፍት ሆና ቆይታለች"
ምዕራባውያኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባለ ሀገራትም "የሩሲያ ደህንነት እና ጠቃሚ ጥቅሟ በአስተማማኝ ሁኔታ በሚጠበቅበት ሀሳብ መስማማት አለባቸው። በኪየቭ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ባሉ ግዛቶች ውስጥ የሩሲያውያን እና የሩሲያኛ ተናጋሪዎች መብቶች ሙሉ በሙሉ መመለስ አለባቸው። በዚህ መሠረት የዩክሬን የደህንነት ዋስትናዎችን ለመወያየት ዝግጁ ነን።" ማለታቸው ይጠቀሳል ።
እነዚህ መሰል በሩሲያ በኩል ስለተሰጡ መግለጫዎች ጥያቄዎች የቀረበላቸውን
ትራምፕ መገደቡን መቀጠል “ጥሩ ሀሳብ ይመስላል” ከማለት ዉጭ የዋሽንግተንን አቋም ማሳወቅ አልፈለጉም ሲሉ ያስነበቡት ሮይተርስ ሞስኮ ታይምስ ናቸዉ ።
#የኔታ_ቲዩብ_ዘጋቢ ፦ #ታዴ_የማመይ_ልጅ

10 months ago