Logo
Getu Temesgen
አሸማጋዮች ተንቀሳቀሱ

📌የጋዛ የሰላም ድርድር ሊጀመር በመሆኑ አሸምጋዮች 'በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ' ትራምፕ አሳሰቡ
#ethiopia | የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛን ጦርነት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚሳተፉት በሙሉ “በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ” አሳስበዋል። ሸምጋዮች በሃማስ እና በእስራኤል መካከል ቀጥተኛ ያልሆነ የሰላም ድርድር ለማድረግ ዛሬ ሰኞ በግብፅ ይገናኛሉ ።

ውይይቱ የሚካሄደው ሃማስ በ20 የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም እቅድ፣ ታጋቾችን ማስለቀቅ እና የጋዛ አስተዳደርን ለፍልስጤም ቴክኖክራቶች ማስረከብን ጨምሮ አንዳንድ ነጥቦች ላይ ከተስማሙ በኋላ ነው፣ነገር ግን በሌሎች ጉዳዮች ላይ ድርድር ለማድረግ እየፈለገ ነው።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አክለውም “ጊዜው ለሰላም ወሳኝ ነው ወይም ብዙ ደም መፋሰስ ይከተላል” ብለዋል። ትራምፕ ቀደም ሲል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ታጋቾቹ “በቅርቡ” መፈታት ይጀምራሉ ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።

በሰላም እቅዳቸው ላይ ስላለው ተለዋዋጭነት ሲጠየቁ ትራምፕ "ተለዋዋጭነት አያስፈልገንም ምክንያቱም ሁሉም ሰው ተስማምቷል ነገር ግን ሁልጊዜ አንዳንድ ለውጦች ይኖራሉ" ብለዋል። "ለእስራኤል ትልቅ ነገር ነው፣ ለመላው አረብ ሀገራት፣ ለአለም ትልቅ ጉዳይ ነው ስለዚህ በጣም ደስተኞች ነን" ሲሉ አክለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሃማስ ለታቀደው የሰላም እቅድ ምላሽ ከሰጠ በኋላ አርብ እለት ትራምፕ እስራኤልን “ የቦምብ ጥቃቱን እንድታቆም” ቢናገሩም የእስራኤል የአየር ጥቃት ግን በጋዛ ቀጥሏል።

የእስራኤል መንግስት ቃል አቀባይ ሾሽ ቤድሮሲያን እሁድ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የተወሰኑ የቦምብ ጥቃቶች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ቢቆሙም በአሁኑ ወቅት የተኩስ አቁም ስምምነት የለም” ብለዋል።

ቤድሮስያን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ " በጋዛ ውስጥ በጦር ሜዳ ሕይወታችሀ ላይ ስጋት ካለ ጥቃት ፈፅሙ" ሲሉ ትዕዛዝ ሰጥተውናል ሲሉ ተደምጠዋል ያለው ዳጉ ጆርናል ነው።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.