ልብ ሰባሪ ዜና ከምዕራብ ጎንደር !
ከጥቂት አመታት በፊት በደረቅ ወደብ ከሱዳን ጋር መገናኛ የነበረና ከፍተኛ የንግድ ልዉዉጥ የገንዘብ እንቅስቃሴ ይደረግበት የነበረዉና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
በትጥቅ የታገዘ ጥቃቶች የኢትዮጵያው "ሊቢያ "በተባለው ከጎንደር መተማ መስመር ህዝብ በጫኑ 10 ተሽከርካሪወች ላይ በተፈፀመ ጥቃት 18 ንፁሀን ሰወች ህይወታቸው ሲያልፍ 30 የሚደርሱት ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተነገረ ።
ከስፍራው በደረሰን መረጃ መሰረት በ23/01/2018 ዓም ከጎንደር መተማ መስመር መንገድ ልዩ ስሙ መቃ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ 2 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ
የጦር መሳሪያ የታጠቁ አካላት በአስር የህዝብ ማመላለሻ መለስተኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ባደረሱት ጥቃት 18 ንፁሀን ሰወች ህይወታቸው ሲያልፍ 30 የሚደርሱት ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጎንደር ሆስፒታልና በሌሎች የህክምና ጣቢያዎች በህክምና ላይ ይገኛሉ ።
ከአሁን በፊት የኔታ ቲዩብ ከአካባቢው ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ መሰረት በዚህ አካባቢ በ16/10/2017 ዓ.ም የታጠቁ አካላት በፈፀሙት ጥቃት ከ16 በላይ ሰዎችም በተመሳሳይ ህይወታቸው ማለፉንና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል በአካባቢው ባለስልጣናት በሚንቀሳቀስበት ወቅት አንዳንዴ እጀባ ቢኖርም በተለይም በዚህ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅት ሃላፊነት የሚወስድ አካል አልተገኘም ።
የዝግጅት ክፍላችን ለሞቱት ነብሳቸውን እንዲምረዉ ለተጎዱት ምህረት እንዲያገኙ እየተመኘ
በዚህ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር የምትገናኝበትን ደረቅ ወደብ ሀገራችን የዉጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ሰሊጥና ሌሎች የቅባት እህሎች አምራች አካባቢ ሁሉም አካል ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ለማስገንዘብ ይወዳል ።

10 months ago