Logo
FIDEL POST NEWS
ያንጎ ኢትዮጵያ እና ጆኒ ራጋ ተፈራረሙ

ያንጎ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ በታላቅ ዝግጅት ተመልሶ ከመጣው አንጋፋው የኢትዮጵያ ድምፃዊ ጆኒ ራጋ ጋር "ውሃ እና እሳት" በተሰኘው አዲስ አልበሙ ላይ አብሮ መስራቱን በኩራት ያስታውቃል። ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳጅ ከሆኑ ድምፃውያን መካከል የአንዱን መመለስ ከማክበሩም በተጨማሪ፣ ያንጎ የአገር ውስጥ ተሰጥኦዎችን እና የባህል መገለጫዎችን ለመደገፍ ያለውን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።

በያንጎ የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ይቅናአለም አበበ ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ፥ "የጆኒ ራጋ ሙዚቃ ሁሌም የኢትዮጵያን መንፈስ እና ነፍስ የሚወክል ነው። ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ በነበረው የድምፃዊው መመለስ ላይ ከእርሱ ጋር በመተባበራችን ትልቅ ክስተትን ከማክበር ባለፈ፣ ያንጎ የአገር ውስጥ ተሰጥኦዎች ማህበረሰብን በማነሳሳት፣ በማስተማር እና በማዋሀድ ባለው ኃይል ላይ ያለውን እምነት ዳግም እያረጋገጥን ነው። ይህ ትብብር ከመዝናኛ በላይ የሆነው ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ጥልቅ ግንኙነት እና ያንጎን የዕለት ተዕለት ሕይወታቸው አካል ላደረጉት አሽከርካሪዎቻችን፣ ደንበኞቻችን እና አድናቂዎቻችን ያለንን ክብር የሚያሳይ ነው" ብለዋል።

ጆኒ ራጋ በበኩሉ፥ "ከያንጎ ጋር ያለው ይህ ትብብር ስለ ዳግም መመለሴ አልበም ብቻ አይደለም፤ ፅናትን፣ ማህበረሰብን እና የኢትዮጵያን ሙዚቃ ጉዞን ስለማክበር ጭምር ነው። ላለፉት 20 ዓመታት፣ የኮንሰርት ጉብኝቶቺ እና የቀጥታ ስርጭት ትርኢቶች ወቅት ከጎኔ ለነበሩኝ ታማኝ አድናቂዎቼ ምስጋና ይገባቸዋል፤ በተለይም ለአርቲስቶች መብት እና በኢትዮጵያ የሮያሊቲ ክፍያ እንዲጀመር በምታገልበት ወቅት ከጎኔ ነበሩ። በ'ውሃ እና እሳት' አልበሜ፣ የተረጋጋ መንፈስን እና አስደሳች በዓላትን የሚተርኩ ታሪኮችን በማጋራት ለሙዚቃ ቤተሰቤ ውለታውን መመለስ እፈልጋለሁ። ከያንጎ ጋር መስራታችን ይህንን ራዕይ በየመንገዱ፣ በጉዟቸው እና በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውስጥ ላሉ ሰዎች ይበልጥ ለማቅረብ ያስችለናል። በጋራ፣ አልበም ብቻ እያወጣን አይደለም፤ የሁላችንም የሆነ የባህል ክስተት እየፈጠርን ነው" ብሏል።

በዚህ አጋርነት ያንጎ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን፣ አሽከርካሪዎችን እና ሰፊውን ማህበረሰብ የጆኒ ራጋን መመለስ በደስታ እንዲቀበሉ እና በ"ውሃ እና እሳት" አልበም እንዲዝናኑ ይጋብዛል። አድናቂዎች ከአልበሙ መውጣት ጋር ተያይዞ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን፣ ልዩ ይዘቶችን እና ልዩ ዝግጅቶችን ለማግኘት የጆኒ ራጋን የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.