በኢትዮጵያ ምግቡን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚያበስለው የሕብረተሰብ ክፍል ከአሥር በመቶ የማይበልጥ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ንጹህ የምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ የሚጠቀመውና ምግቡን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚያበስለው የሕብረተሰብ ክፍል ከአሥር በመቶ የማይበልጥ መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚንስቴር ገለጸ። በመሆኑም በዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለማቃለልና የኢትዮጵያን የኢነርጂ ዘርፍ የተሻለና የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ሪፎርም እንደሚያስፈልገውም ተገልጿል።
በጉዳዩ ላይ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር፣ ኢ/ር) ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት በኢነርጂው ዘርፍ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበች መሆኗን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ አሁንም በዘርፉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል። በዚህ የተነሳም እንደሀገር የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቀሚው የህብረተሰብ ክፍል 54 በመቶ ብቻ ሆኗል።
በዚህም ምግቡን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚያበስለው ወይንም ንጹህ የምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚው የሕብረተሰብ ክፍልም ከአሥር በመቶ የማይበልጥ መሆኑንና ቀሪዉ 90 በመቶ የሕብረተሰብ ክፍል ለምግብ ማብሰያነት የሚጠቀመው ባዮማስ ወይም የእንጨት ማገዶ መሆኑን አመላክተዋል።
seledadotio

10 months ago