የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ደህንነት በራቃቸው ከተሞች እንደማይካሄዱ ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ
#ethiopia | የአሜሪካው ዶናልድ ትራምፕ የ2026 ዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታዎችን ደህንነት የራቃቸው ናቸው ብለው ከሚያስቧቸው ከተሞች እንደሚቀይሩ ተናግረዋል።
በሚቀጥለው ዓመት ክረምት ላይ 48 ቡድኖች የሚጋጠሙበትን የዓለም ዋንጫ 11 የአሜሪካ ከተሞች ለማስተናገድ ተዘጋጅተዋል።
የ2026 የዓለም ዋንጫን ካናዳ እና ሜክሲኮ አሜሪካ በጋራ እንደሚያሰናዱም ይታወቃል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኦቫል ኦፊስ ለተገኙ ጋዜጠኞች "ይህ ለዓለም ዋንጫ መልካም ነው፤እኔ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም ብዬ ካሰብኩ ወደ ሌላ ከተማ እናዞረዋለን" ሲሉ ተናግረዋል።
የዓለም ዋንጫን የሚያስተናግዱት 11 ከተሞች አትላንታ፣ ቦስተን፣ ዳላስ፣ ሂውስተን፣ ካንሳስ ሲቲ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ማያሚ፣ ኒው ዮፕሬዚዳንትርክ/ኒው ጀርሲ፣ ፊላደልፊያ፣ ሳንፍራንሲስኮ እና ሲያትል ናቸው።
ትራምፕ ጥያቄ የቀረበላቸው በዲሞክራቶች በሚመሩት ሲያትል እና ሳን ፍራንሲስኮ ስለሚካሄዱ ጨዋታዎች ነበር።
ሁለቱም ከተሞች ስድስት ጨዋታዎችን እንደሚያዘጋጁ የወጣው ድልድል ያሳያል።
ትራምፕ በተደጋጋሚ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚታዩ ወንጀሎችን መቅረፍ የአጀንዳቸው ማዕከል መሆኑን ይናገራሉ።
መረጃው የቢቢሲ ስፖርት ነው፡፡
#hagerie #sport #gtmc

9 months ago