Logo
FIDEL POST NEWS
የ2018 ዓ/ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ ተደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 - 25/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል።

አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.... በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘውትር በስራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ ngatethernet.edu.et በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስቧል።

የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በTeleBirr በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርበት አክሏል።

#moe
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.