Logo
Getu Temesgen
በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ ትኩረት ያደረጉ አራት መጸሐፍት ተመረቁ
#ethiopia | የኦሮሞ ህዝብ እንደሌሎቹ ወንድም ህዝቦች ሁሉ በኢትዮጵያ ሀገርነት ላይ አስተዋጽኦ ያደረገ ታላቅ ህዝብ ነው።ይህ የሀገር የማንነት መዝገብ ውስጥ በወርቃማ ብዕር ተጽፎ ያለ እውነት ነው።

ህዝብ ሀገር በምትባል ጣሪያ ስር ሲኖሩ አንዱ ብሔር ከአንዱ ሳይበልጥ፤ሳያንስም ጭምር ተከብሮ ይኖር ዘንድ ያስፈልጋል።

ታድያ ይሄኑኑ ምልከታ የሚያጠናክሩ በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ ትኩረት ያደረጉ አራት መጸሐፍት የተሰናዱ ሲሆን ዛሬ ለንባብ በቅተዋል።

የተከበሩ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ሸመልስ አብዲሳን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአራቱ ጣምራ መጽሐፍት ምረቃ ላይ የተገኙ ሲሆን መጽሐፍቶቹ የኦሮሞን አጠቃላይ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት የሰነዱ መጽሐፍ ተብሏል።

በሶስት ቋንቋዎች ለንባብ የበቃው ፊንፊኔ ትናንት እና ዛሬ የተሰኝው መፅሐፍ የኦሮሞ ህዝብ በማንነቱ ፊንፊኔን ጨምሮ በየትኛውም የአገሪቱ አከባቢዎች ተከብሮ በእኩልነት ይኖር ዘንድ የተገባ መሆኑን የሚያትት ሲሆን ከትናንት ዛሬ በርካታ ነገሮች መሻሻላቸውን ይገልፃል።

በ14 ምሁራን ተዘጋጅቶ በኦሮሞ የምርምር ማህበር የህትመት ብርሃን ለማየት የበቁት መጽሐፍት ከስር የተዘረዘሩት ሲሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ገበያ ላይ ውለዋል ተብሏል።

1. Finfinnee Past and Present, (English, Afan Oromoo, Amharic)

2. A Partially Annotated Bibliography of Oromoo

3. In search of Knowledge: some issues and Perspective on Oromo studies

4. The Gada system of Governance (Seera Caffee Oromoo)

በምረቃው መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያው ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ''የኦሮሞ ምሁራንን የሚጽፏቸው መጽሐፍት ከማሳተም ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎች እናደርጋለን፤ '' ብለዋል።

በተጨማሪም ከአቶ ሽመልስ እጅ ለቁቤ አስተዋጽኦ ያደረጉ የሀገር ሽማግሌ 250 ሺ ብር የገንዘብ ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን ለመጽሐፍቱ ህትመት አስተዋጽኦ ያደረጉ የተለያዩ ግለሰቦችን አና ተቋማትን የምስክር ወረቀት አና ዋንጫ ተሸልመዋል።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.