Logo
YenetaTube
አሁንም ቀኝ እጁ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች

ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በተጣራሪነቱ ይታወቃል፡፡

በቀዳሚ ስሙ “ዲዲሞስ” ወይም ጨለማ የሚባል ስም ቢኖረውም በኋላ ግን ቶማስ ወይም ፀሐይ ተብሏል፡፡ ቅዱስ ቶማስ ሲጠራ በትንሣኤ ሙታን ከማያምኑት ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር ከወገኖቹ የወሰደውን ትምህርት ይዞ ጌታችን ከሙታን በተነሳ ጊዜ እጆቹን ካልዳሰስኩ በጦር የተወጋ ጎኑን ካልነካሁ አላምንም ብሎ ዳሶ ካረጋገጠ በኋላ ግን ጌታዬ አምላኬ ብሎ ሰግዷል፡፡ ቶማስ አንድን ነገር ለመቀበል በቂ እውቀት የሚፈልግ ሲሆን ላመነበት ነገርም ቆራጥ የሆነ ሐዋርያ ነው። ቶማስ ክርስቶስን መከተል ሞትን እንደሚያስከትል አውቆ ዋጋ ተምኖ የሚጓዝ ከክርስቶስ ጋር ለመሞትም ዝግጁነቱን የገለጠ፣ ደፍሮ ሌሎችንም በማደፋፈር የሚታወቅ ሐዋርያ ነው። ሕይወቱንም አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ ሆኖ የተከተለው ሐዋርያ መሆኑ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይገለጻል።

ከቅዱሳን ሐዋርያት ስለክርስቶስ ፍቅር ያልተሰዋ የለም፤ የእርሱ ግን ገና የመከራው ጊዜ ከመምጣቱ በፊት የታየ ነው፡፡ በዮሐንስ 11÷16 እንደተጻፈው ጌታ ወደ አልዓዛር መቃብር እንደሚሄድ በተናገረ ጊዜ “ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ” አለ፡፡ እመቤታችን ስታርግም ከሁሉም ቀድሞ ያየው እርሱ ነው፡፡ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ የገባው እንደ ባሪያ በ30 ብር ተሽጦ ነበር፡፡ የገባበት አካባቢ አስተዳዳሪ ሉክዮስ በቤቱ ሲያገለግል ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እንደሚችል ስለነገረው ብዙ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሕንጻ ሰርቶ እንዲጠብቀው ነግሮት የተለየ ጥበብኛ ሰው አገኘሁ ለማለት ወደ ንጉሥ ሄደ፡፡ ቅዱስ ቶማስ ግን ገንዘቡን ለነዳያን መጸወተው በርካቶችንም አስተምሮ አሳምኗቸዋል፡፡ የሉክዮስ ሚስትና ልጆቿ ቤቱ ካሉ አገልጋዮች ጋር ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

ሉክዮስ ከሄደበት ተመልሶ ሕንጻውንና ሐውልቶቹን ለማየት ቢፈልግም ሐዋርያው በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንጻዎች እኒህ ናቸው ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ መልቶ አሸክሞ በገበያው ሲያዞረው ሚስቱ አርሶንዋ አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡ መስፍኑም ደንግጦ ሚስቴን ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለሁ አለው፡፡ ጌታ ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነሥታለች በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠምቋል፡፡ ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡ በቀንጦፍያ የተገደሉ የአንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆች ስልቻውን እያስነካ አስነሥቶለታል፡፡

በኢናስም የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሱ ሚስት ጀምሮ እስከ ተራ ገባር ድረስ ያሉት ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ በኋላም የጣኦት ካህናተ በተንኮል ከንጉሥና መኳንንቱ ጋር አጣልተው በሰይፍ አስመትተውታል፡፡ ዛሬም ድረስ ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ ቅድስት ቀኝ እጅ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡ ገዳማውያን ቅዱሳኑን አብነት አድርገው በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ እንኳን አልፈው በእምነታቸው ጸንተው የክርስቶስን ወንጌል በሕይወታቸው ሰብከው፣ ወንጌልን ኖረው ያልፋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታችውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊዎች እንሆናለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.