Logo
YenetaTube
ኦሮምኛን ለመፃፍ ከላቲን ይልቅ ግዕዝ ይቀላል /ጥናት/ በእርግጥ ጠቃሚ ነገሮች አይነበቡም

‎በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያ በኦሮሞው ተወላጅ በታላቁ ወንጌላዊው ኦኔሲሞስ ነሲብ መፅሐፍ ቅዱስን ከላቲን ይልቅ በግዕዝ ፊደላት በመፃፋ "መጫፈ ቁልቁሉ "ተብሎ በራሳችን ቋንቋ መታተሙን ታዉቃላችሁ ?

‎ከላቲን ፊደላት ይልቅ ኦሮምኛ በኢትዮጵያ ቀለማት ቢፃፉ የተሻለ ፣ ቀልጣፋ እና ጊዜ እና ገንዘብ ቆጣቢ እንደሆነ በኦሮሚያዊትዋ ልጅ፣ በሰንዳፋው ተወላጅ በዶክተር አበራ ሞላ መላ በመዘየድ በኢትዮጵያ ፊደላት ተቀርፀው በተግባር ለመዋል ማስቻላቸዉንስ ?።

‎ዶክተር አበራ ሞላ ለበርካታ አመታት ባደረጉት የምርምር ውጤት የኢትዮጵያ ፊደላት ኦሮምኛን ለመክተብ ብቁ ከመሆናቸውም በላይ ብዙ ጥቅም ያላቸው መሆናቸውን የሚመሰክሩ ሰነዶች ተዘጋጅተዋል። ዊኪፔድያ ውስጥ ገብተው መገኘት ይችላሉ ።

‎ከግእዝ እና ከላቲን ፊደል የትኛው ይበልጥ ውጤታማና ብቁ እንደ ሆነ እንመልከት ከተባለም
‎Uummanni Oromoo ilmaan namaa biyya lafaa የሚለዉን ግእዝ "ኡመኒ ኦሮሞ ኢልማን ነማ ብያ ለፋ "
‎Kanarratti Uumaman kessaa tokkodha Biyyi

‎ከነረቲ ኡመመን ኬሳ ቶኮዳ ብዪ
‎Uumamaa fii jireenya issa Aafrikaa Bahaa

‎ኡመማ ፊ ጅሬኘ ኢሳ አፍሪካ በሃ
‎Gara kaabaatti Yemmuu ta’u Uummmata
‎ገረ ካባቲ የሙ ተኡ ኡመተ

‎Akata Sabaatti baay’ina gudda qabu kan
‎አከ ሳባቲ የሙ ተኡ ኡመተ
‎Baha gaanfa Aafrikaatti argamu keessaa

‎ኦሮምኛን ለመጻፍ ከላቲኑ እና ከኢትዮጵያው ፊደል የትኛው ብቁ፣ ቀልጣፋ እና ጊዜ እና ገንዘብ ቆጣቢ እንደሆነ እንይ፤ Uummanni Oromoo ilmaan namaabiyya lafaa
‎“Uumamaa” የሚለው ቃል በላቲን ሲጻፍ 7 ሆህያት ፈጅቷል፡፡ በኢትዮጵያው ግን “ኡመማ” ተብሎ በ3 ፊደላት ይጻፋል፡፡
‎“oromoo” የሚለው ቃል በላቲን 6 ሆህያት አሉት፡፤ በግዕዝ ግን “ኦሮሞ” ተብሎ በ 3 ሆህያት ይጻፋል፡፡
‎ “ilmaan” የሚለው በላቲን 6 ሆሄያት አሉት፤ በግዕዝ ግን አራት በቂው ነው፡፡
‎ “namaa፣ biyya፣ lafaa፣” የሚሉትም ቃላት በላቲኑ እያንዳንዳቸው 5 ሆሄያት ፈጅተዋል፡፡
‎በግዕዙ ቢሆን ግን “ነማ፣ ቢያ፣ ለፋ” ተብለው እያንዳንዳቸወቅ በ 2 ፊደላት ይጻፋሉ፡፡

‎ኦሮምኛን ለመጻፍ ከላቲኑ እና ከኢትዮጵያው ፊደል የትኛው ብቁ፣ ቀልጣፋ እና ጊዜ እና ገንዘብ ቆጣቢ እንደሆነ እንይ፤ Uummanni Oromoo ilmaan namaabiyya lafaa
‎“Uumamaa” የሚለው ቃል በላቲን ሲጻፍ 7 ሆህያት ፈጅቷል፡፡ በኢትዮጵያው ግን “ኡመማ” ተብሎ በ3 ፊደላት ይጻፋል፡፡ “oromoo” የሚለው ቃል በላቲን 6 ሆህያት አሉት፡፤ በግዕዝ ግን “ኦሮሞ” ተብሎ በ 3 ሆህያት ይጻፋል፡፡ “ilmaan” የሚለው በላቲን 6 ሆሄያት አሉት፤ በግዕዝ ግን አራት በቂው ነው፡፡ “namaa፣ biyya፣ lafaa፣” የሚሉትም ቃላት በላቲኑ እያንዳንዳቸው 5 ሆሄያት ፈጅተዋል፡፡ በግዕዙ ቢሆን ግን “ነማ፣ ቢያ፣ ለፋ” ተብለው እያንዳንዳቸወቅ በ 2 ፊደላት ይጻፋሉ፡፡

‎ከላቲን ይልቅ፣ በኢትዮጵያዊው ግእዝ ፊደል ኦሮምኛ ቢፃፍ እጅግ በርካታ ፋይዳዎች አሉት ያሉት (ከፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ)

‎ግእዝ ባለፉት 4000 ዐመታት ከሁላችንም አባት ከኢትዮጵ ጀምሮ በነገሥታት ልጅ ልጆቹ እየተቀረፀና እየተሻሻለ ሲወርድ ሲዋረድ እዚህ የደረሰ ነው።

‎የኢትዮጵያ ፊደላት የሰሜን ሰዎች እና የአማራ ብቻ አይምሰለን።

‎ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አጋዝያን መደበኛ ፊደላቱን ኢትዮጵያ ውስጥ አግኝተው ለራሳቸው እንዲመቻቸው አድርገው ሞርደዋቸዋል። አማሮች ዘመዶቻችንም ለእነሱ አፍ የሚስማሙ የተወሰኑ ፊደላትን ቀርፀው እውስጣቸው አካተዋል። ስለዚህ ፊደላቱ የኦሮሞም ናቸው። በእርግጥም ናቸው እንጂ ባይሆኑም እንኳ ከማናውቃቸው ከባእዳኑ ከአውሮፓውያኖቹ ፊደላት ይልቅ የተፈጠርንበት እና የኖርባት የኢትዮጵያ ፊደላት ለኛ ይቀርቡናል። ሲሉ ረጂም ጥናታዊ ፅሁፍ ጎግል ላይ ታገኙታላችሁ ።


ታዴ የማመይ ልጅ

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.