1 month ago
የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ እንዲተዳደር ተወሰነ
*******************
የአማራ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በብሔራዊ ፓርኮች የአስተዳደር ሥርዓት እንዲመራ የቀረበውን የደንብ ረቂቅ ሙሉ በሙሉ አጽድቋል።
የአማራ ክልል የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ እንደገለጹት፤ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ከ8 ሺህ 732 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው ሲሆን፣ በአንኮበር፣ በባሶና ወራና እንዲሁም በጣርማ በር ወረዳዎች በሚዋሰኑ 15 የገጠር ቀበሌዎች የተከበበ ደን ነው።
ጥብቅ ደኑ የበርካታ ብዝኃ-ሕይወት ሀብቶች መኖሪያ በመሆኑ፣ ጥበቃና ልማት እየተደረገለት ወደ ብሔራዊ ፓርክነት እንዲያድግ ተከታታይ ሳይንሳዊ ጥናቶች ሲካሄዱበት መቆየታቸውን ኃላፊው አብራርተዋል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጥብቅ ደኑ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት መሠረት በማድረግ በርካታ የጥበቃና የልማት ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የገለጹት አቶ ተስፋሁን፤ ስፍራው በክልሉና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ጋር እኩል ጥበቃና ልማት እንዲደረግለት የሚያስችል የጥበቃና ልማት ደንብ በማዘጋጀት ለክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት አቅርበው ሲያስፈጽሙ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
አካባቢው በብሔራዊ ፓርክነት በይፋ ተመዝግቦ የቀጣይ የቱሪዝም ተስፋ እንዲሆን ውሳኔ በመተላለፉ፣ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ለክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
የአማራ ክልል የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ አምስት ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሰባት የማኅበረሰብ ጥብቅ ስፍራዎችን በበላይነት በማስተዳደር የጥበቃና ልማት ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አሚኮ ዘግቧል።
#ethiopia #northshewa #wofwashapark #nationalpark #biodiversity #ecotourism

Comments