3 months ago
አሜሪካ ለመግባት በሚያስገድድደው የ15 ሺሕ ዶላር የገንዘብ ማስያዣ ደንብ ኢትዮጵያ ተካተተች
#ethiopia | የዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር፣ ወደ አሜሪካ መግባት በሚፈልጉ የተወሰኑ ሀገራት ዜጎች ላይ አዲስ የገንዘብ ማስያዣ መመሪያ ማውጣቱን የጀርመን ድምፅ ዘግቧል። ይህ መመሪያ ከመጪው መጋቢት 24 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ተገልጿል።
የደንቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የገንዘብ መጠኑ፦ መመሪያው የሚመለከታቸው ሀገራት ዜጎች የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ከሌሎች መስፈርቶች በተጨማሪ 15,000 ዶላር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
* የቪዛ ዓይነቶች፦ ማስያዣው ግዴታ የሚሆነው ለሥራ (B1) እና ለጉብኝት (B2) ቪዛ አመልካቾች ላይ ነው።
* የተካተቱ ሀገራት፦ መጀመሪያ ላይ የ38 ሀገራት ዜጎችን ብቻ ይለይ የነበረው ዝርዝር፣ አሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች 12 ሀገራት ዜጎች ተካተውበታል። በአጠቃላይ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት የ50 ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
* የገንዘብ አመላለስ፦ ተጓዦች ቆይታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ያስያዙት ገንዘብ እንደሚመለስላቸው ተጠቁሟል።
ይህ አዲስ አሰራር በተለይ በጎብኝዎችና በንግድ ተጓዦች ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ከፍተኛ እንደሚሆን እየተነገረ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #usa #visapolicy #ethiopia #travelnews #usvisa #breakingnews #africa #donaldtrump

Comments