22 days ago
ለ30 ደቂቃ ያህል ባቡሩን ያስቆመው "ዝንብ"
#ethiopia | በጃፓን እጅግ በጣም ፈጣንና የሰከንድ መዘግየት የማይታይበት ባቡር ሳይታሰብ ለ30 ደቂቃዎች እንዲቆም ተገዷል።
የባቡሩ መቆም ምክንያት ደግሞ ከውጭ የመጣች አንዲት ትንሽ ዝንብ በሾፌሩ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ ገብታ የሾፌሩን ትኩረት በማሳጣቷ ነው።
በሰዓት አክባሪነቱ እና በከፍተኛ ፍጥነቱ የሚታወቀው የጃፓን የመንገደኞች ባቡር በዕለቱ ባልተጠበቀ እና ባልተለመደ ምክንያት ለ30 ደቂቃ ያህል ጉዞውን ለማቋረጥ ተገዷል።
ለዚህ የመዘግየቱ ምክንያት ደግሞ በቴክኒክ ችግር ሳይሆን በሾፌሩ የቁጥጥር ክፍል ውስጥ የገባች አንዲት ትንሽ ዝንብ ናት።
ጉዞው በተለመደው ፍጥነት እና ደህንነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ይህች ትንሽ ዝንብ የሾፌሩ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ ሰርጎ በመግባት የሾፌሩን ሙሉ ትኩረት ማሳጣቷን ነው የተገለፀው።
በከፍተኛ ፍጥነት በሚጓዝ ባቡር ውስጥ የአንድ ሰከንድ የትኩረት ማጣት ወይም ስህተት ለከፍተኛ አደጋ ሊዳርግ ስለሚችል ሾፌሩ ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ባቡሩን በአቅራቢያው ባለው ማቆሚያ ላይ በአስቸኳይ ለማቆም መገደዱን አሳውቋል።
የባቡር ድርጅቱ ባወጣው ኘግለጫ ለደህንነት ሲባል ነው ባቡሩ ያስቆምነው ቢልም ተሳፋሪዎች ግን በሁኔታው ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ሆኖም የባቡሩ ጥገና እና የደህንነት ቡድን አባላት የመቆጣጠሪያ ክፍሉን ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ማድረጋቸውን ካረጋገጡ በኋላ ባቡሩ ጉዞውን ቀጥሏል።
አጋጣሚው በጃፓን የትራንስፖርት ታሪክ ውስጥ ያልተለመደ እና የብዙዎችን ትኩረት የሳበ አስገራሚ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #japanbullettrain #shinkansen #japannews #oddnews #breakingnews #japantransport #shorts #reels #viralnews

ከ3 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የወረሰችው ባለጠጋዋ ድመት!
#ethiopia | በጣሊያን አንዲት ሀብታም አዛውንት ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት ያፈሩትን ሙሉ ሀብትና ንብረት "ኮኮ" ለምትባል ተወዳጅ ድመታቸው ማወረሳቸው በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
የሟቿ ቤተሰቦችና የህግ አማካሪዎች እንደገለፁት ሴትዮዋ በህይወት በነበሩበት ወቅት ለድመታቸው የነበራቸው ፍቅርና ቁርኝት እጅግ ከፍተኛ ነበር።
በመሆኑም ከሞታቸው በፊት ባደረጉት ህጋዊ የኑዛዜ ውል መሠረት ከ3 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የሚያወጣው ንብረታቸው በሙሉ ለዚችው እድለኛ ድመት እንዲተላለፍ ወስነዋል ብለዋል።
በኑዛዜው መሠረት ኮኮ ለብቻዋ የተመደበላት ሰፊና ቅንጡ ቪላ ቤት ውስጥ የምትኖር ይሆናል።
የቤቱ እንክብካቤና ጥገና ሙሉ በሙሉ ከዚሁ የውርስ ገንዘብ የሚሸፈን እንደሆነም ተገልጿል።
የድመቷን ዕለታዊ ምግብ፣ ጤና እና መዝናናት የሚከታተሉ የሙሉ ጊዜ የግል ሞግዚቶች የተቀጠሩላት ሲሆን ደህንነቷን የሚያስጠብቁ የግል ጥበቃዎችም ተመድበውላታል።
ኮኮ የምትመገበው በልዩ ባለሙያዎች የሚዘጋጅ ከፍተኛ ጥራት ያለው ምግብ ሲሆን በየጊዜው በእንስሳት ህክምና ባለሙያዎች የጤና ክትትል ይደረግላታል።
በጣሊያን ህግ መሠረት እንስሳት በቀጥታ የሀብት ባለቤት መሆን ባይችሉም ባለሀብቶች ንብረታቸውን ለእንስሳቱ እንክብካቤ የሚውል አደራ ጠባቂ ድርጅት ወይም ግለሰብ በመሰየም ማውረስ ይችላሉ።
በዚህም መሠረት የኮኮ ሀብት በህጋዊ ተወካዮች የሚተዳደር ሲሆን ገንዘቡ የሚወጣው ለድመቷ ቀሪ የህይወት ዘመን አስፈላጊ ለሆኑ ማንኛቸውም ወጪዎች ብቻ ነው ተብሏል።
ኮኮ በተፈጥሮ ሞት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ቀሪው ገንዘብ ለእንስሳት መብት ተሟጋች ድርጅቶች ወይም በኑዛዜው ላይ ለተጠቀሱ በጎ አድራጎት ተቋማት እንደሚተላለፍ ታውቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #richcat #catmillionaire #trendingnews #viralnews #italycat #luxurylife #catinheritance #oddnews #worldnews

24 days ago
"እባክህን ቤትህን አጽዳ!"
#ethiopia | ሌባው ወደ ቤት ገብቶ ዕቃ ከመስረቅ ይልቅ ቤቱን አጽድቶ ወጥቷል።
በእንግሊዝ አንድ ሌባ ወደ አንድ ቤት ገብቶ ዕቃዎችን ለመስረቅ ሲፈልግ ቤቱ በጣም የተዝረከረከ ሆኖ ያገኘዋል።
ሌባው መስረቁን ትቶ በመጀመሪያ በቤቱ ውስጥ ያሉትን ልብሶች ያጥባል የቆሸሹትን ሳህኖች አጥቦ ያስቀምጣል በመጨረሻም ወለሉን በቫክዩም ክሊነር ይጠርጋል።
የቤቱ ባለቤት ሲመጣ ቤቱ ተጠርጎና አምሮ ሲያየው ደንግጦ የተፈጠረውን መመልከት ጀመረ።
ሌባው ግን ምንም ሳይሰርቅ ማስታወሻ ብቻ ጽፎ ሄደ "እባክህን ቤትህን አጽዳ!" የሚል።
በኋላ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ግለሰብ በፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ በመባሉ የ19 ወራት የእስራት ፍርድ ተፈርዶበታል።
ክስተቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙሃን መገናኛዎች እና በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ትልቅ መነጋገርያ እና አስገራሚ ዜና ለመሆን ችሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #uknews #bizarrenews #viralnews #damianwojnilowicz #cleaningburglar

1 month ago
የእናቷ ሞት ትውስታ የዜና አቅራቢነቷን አስረሳት
#ethiopia | የFox 5 ዜና አቅራቢዋ ሮዚና ስኮት እናቷ ማሪዮን በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በቀጥታ ስርጭት ስቱዲዮ ስትመለስ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷታል።
ለረጅም ዓመታት በጠንካራ የጋዜጠኝነት ሙያዋ እና በተረጋጋ አቀራረቧ የምትታወቀው ሮዚና የእናቷን ህልፈት እና ከእሷ ጋር ያሳለፈቻቸውን ውብ ትዝታዎች ዜና ማቅረቧን አስረስተዋታል።
በወቅቱ የነበረው ሁኔታ የስቱዲዮ ፕሮቶኮልን አልፎ የእናትነትን ታላቅ ቦታ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ አጋጣሚ ነበር።
እንደዚሁም ሙያዊ ድንበር ሰብሮ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ስሜት ጎልቶ የታየበት ነበር።
የስራ ባልደረቦቿም በስቱዲዮ ውስጥ ድጋፋቸውን እና አጋርነታቸውን የገለጹላት ሲሆን ክስተቱን በቀጥታ ስርጭት የተከታተሉ በርካታ ተመልካቾችም ለሮዚና ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
አጋጣሚው በጋዜጠኝነት ሙያዊ ስነ ምግባር አጥር ውስጥ የማይታጠረውን እውነተኛውን የሰው ልጅ የተፈጥሮ ስሜት እና የሃዘን ግዝፈት ጎልቶ ያሳየ ክስተት ሆኖ ታይቷል።
በመጨረሻም በቴሌቪዥን መስኮት ላይ በቀጥታ ስርጭት እያለቀሰች ለተመልካቾች ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን የሥራ ባልደረቦቿም አቅፈው አጽናንተዋታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #fox5news #rosannascotto #humaninterest #viralnews #media #journalist #emotion

4 months ago
በትዳር ፍቺ የተበሳጨው ግለሰብ የራሱን ባለ ሁለት ፎቅ ቤት በኤክስካቫተር መናዱ ተሰማ
#ethiopia | በሮማንያ ባለቤቱ የፍቺና የንብረት ክፍፍል ጥያቄ በማንሳቷ የተበሳጨ አንድ ግለሰብ፣ ንብረቱን ላለማካፈል ሲል ለብዙ ዓመታት የኖሩበትን ባለ ሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት በኤክስካቫተር ሙሉ በሙሉ አፍርሷል።
"የኔ ካልሆነ ለማንም አይሆንም" በሚል እልህ የተፈጸመውና በጎረቤቶች በቪዲዮ የተቀረጸው ይህ ድርጊት በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ግለሰቡ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በማናጋቱ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፣ የሕግ ባለሙያዎች ድርጊቱ ካጋለጠው ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ ለቀድሞ ባለቤቱ የሚከፍለውን የካሳ ክፍያ እንደሚያስከትልበት ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#romania #divorcedispute #oddnews #propertydamage #viralnews #oddstory

Comments