22 days ago
ከ3 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የወረሰችው ባለጠጋዋ ድመት!
#ethiopia | በጣሊያን አንዲት ሀብታም አዛውንት ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት ያፈሩትን ሙሉ ሀብትና ንብረት "ኮኮ" ለምትባል ተወዳጅ ድመታቸው ማወረሳቸው በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
የሟቿ ቤተሰቦችና የህግ አማካሪዎች እንደገለፁት ሴትዮዋ በህይወት በነበሩበት ወቅት ለድመታቸው የነበራቸው ፍቅርና ቁርኝት እጅግ ከፍተኛ ነበር።
በመሆኑም ከሞታቸው በፊት ባደረጉት ህጋዊ የኑዛዜ ውል መሠረት ከ3 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የሚያወጣው ንብረታቸው በሙሉ ለዚችው እድለኛ ድመት እንዲተላለፍ ወስነዋል ብለዋል።
በኑዛዜው መሠረት ኮኮ ለብቻዋ የተመደበላት ሰፊና ቅንጡ ቪላ ቤት ውስጥ የምትኖር ይሆናል።
የቤቱ እንክብካቤና ጥገና ሙሉ በሙሉ ከዚሁ የውርስ ገንዘብ የሚሸፈን እንደሆነም ተገልጿል።
የድመቷን ዕለታዊ ምግብ፣ ጤና እና መዝናናት የሚከታተሉ የሙሉ ጊዜ የግል ሞግዚቶች የተቀጠሩላት ሲሆን ደህንነቷን የሚያስጠብቁ የግል ጥበቃዎችም ተመድበውላታል።
ኮኮ የምትመገበው በልዩ ባለሙያዎች የሚዘጋጅ ከፍተኛ ጥራት ያለው ምግብ ሲሆን በየጊዜው በእንስሳት ህክምና ባለሙያዎች የጤና ክትትል ይደረግላታል።
በጣሊያን ህግ መሠረት እንስሳት በቀጥታ የሀብት ባለቤት መሆን ባይችሉም ባለሀብቶች ንብረታቸውን ለእንስሳቱ እንክብካቤ የሚውል አደራ ጠባቂ ድርጅት ወይም ግለሰብ በመሰየም ማውረስ ይችላሉ።
በዚህም መሠረት የኮኮ ሀብት በህጋዊ ተወካዮች የሚተዳደር ሲሆን ገንዘቡ የሚወጣው ለድመቷ ቀሪ የህይወት ዘመን አስፈላጊ ለሆኑ ማንኛቸውም ወጪዎች ብቻ ነው ተብሏል።
ኮኮ በተፈጥሮ ሞት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ቀሪው ገንዘብ ለእንስሳት መብት ተሟጋች ድርጅቶች ወይም በኑዛዜው ላይ ለተጠቀሱ በጎ አድራጎት ተቋማት እንደሚተላለፍ ታውቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #richcat #catmillionaire #trendingnews #viralnews #italycat #luxurylife #catinheritance #oddnews #worldnews

Comments