22 days ago
ለ30 ደቂቃ ያህል ባቡሩን ያስቆመው "ዝንብ"
#ethiopia | በጃፓን እጅግ በጣም ፈጣንና የሰከንድ መዘግየት የማይታይበት ባቡር ሳይታሰብ ለ30 ደቂቃዎች እንዲቆም ተገዷል።
የባቡሩ መቆም ምክንያት ደግሞ ከውጭ የመጣች አንዲት ትንሽ ዝንብ በሾፌሩ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ ገብታ የሾፌሩን ትኩረት በማሳጣቷ ነው።
በሰዓት አክባሪነቱ እና በከፍተኛ ፍጥነቱ የሚታወቀው የጃፓን የመንገደኞች ባቡር በዕለቱ ባልተጠበቀ እና ባልተለመደ ምክንያት ለ30 ደቂቃ ያህል ጉዞውን ለማቋረጥ ተገዷል።
ለዚህ የመዘግየቱ ምክንያት ደግሞ በቴክኒክ ችግር ሳይሆን በሾፌሩ የቁጥጥር ክፍል ውስጥ የገባች አንዲት ትንሽ ዝንብ ናት።
ጉዞው በተለመደው ፍጥነት እና ደህንነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ይህች ትንሽ ዝንብ የሾፌሩ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ ሰርጎ በመግባት የሾፌሩን ሙሉ ትኩረት ማሳጣቷን ነው የተገለፀው።
በከፍተኛ ፍጥነት በሚጓዝ ባቡር ውስጥ የአንድ ሰከንድ የትኩረት ማጣት ወይም ስህተት ለከፍተኛ አደጋ ሊዳርግ ስለሚችል ሾፌሩ ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ባቡሩን በአቅራቢያው ባለው ማቆሚያ ላይ በአስቸኳይ ለማቆም መገደዱን አሳውቋል።
የባቡር ድርጅቱ ባወጣው ኘግለጫ ለደህንነት ሲባል ነው ባቡሩ ያስቆምነው ቢልም ተሳፋሪዎች ግን በሁኔታው ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ሆኖም የባቡሩ ጥገና እና የደህንነት ቡድን አባላት የመቆጣጠሪያ ክፍሉን ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ማድረጋቸውን ካረጋገጡ በኋላ ባቡሩ ጉዞውን ቀጥሏል።
አጋጣሚው በጃፓን የትራንስፖርት ታሪክ ውስጥ ያልተለመደ እና የብዙዎችን ትኩረት የሳበ አስገራሚ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #japanbullettrain #shinkansen #japannews #oddnews #breakingnews #japantransport #shorts #reels #viralnews

Comments