1 month ago
የእናቷ ሞት ትውስታ የዜና አቅራቢነቷን አስረሳት
#ethiopia | የFox 5 ዜና አቅራቢዋ ሮዚና ስኮት እናቷ ማሪዮን በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በቀጥታ ስርጭት ስቱዲዮ ስትመለስ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷታል።
ለረጅም ዓመታት በጠንካራ የጋዜጠኝነት ሙያዋ እና በተረጋጋ አቀራረቧ የምትታወቀው ሮዚና የእናቷን ህልፈት እና ከእሷ ጋር ያሳለፈቻቸውን ውብ ትዝታዎች ዜና ማቅረቧን አስረስተዋታል።
በወቅቱ የነበረው ሁኔታ የስቱዲዮ ፕሮቶኮልን አልፎ የእናትነትን ታላቅ ቦታ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ አጋጣሚ ነበር።
እንደዚሁም ሙያዊ ድንበር ሰብሮ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ስሜት ጎልቶ የታየበት ነበር።
የስራ ባልደረቦቿም በስቱዲዮ ውስጥ ድጋፋቸውን እና አጋርነታቸውን የገለጹላት ሲሆን ክስተቱን በቀጥታ ስርጭት የተከታተሉ በርካታ ተመልካቾችም ለሮዚና ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
አጋጣሚው በጋዜጠኝነት ሙያዊ ስነ ምግባር አጥር ውስጥ የማይታጠረውን እውነተኛውን የሰው ልጅ የተፈጥሮ ስሜት እና የሃዘን ግዝፈት ጎልቶ ያሳየ ክስተት ሆኖ ታይቷል።
በመጨረሻም በቴሌቪዥን መስኮት ላይ በቀጥታ ስርጭት እያለቀሰች ለተመልካቾች ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን የሥራ ባልደረቦቿም አቅፈው አጽናንተዋታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #fox5news #rosannascotto #humaninterest #viralnews #media #journalist #emotion

Comments