6 months ago
አሜሪካ የሆርሙዝ ሰርጥን እየዘጋች ነው
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እጅግ ወሳኝ በሆነው የሆርሙዝ የባህር መስመር ላይ የአሜሪካ ባህር ኃይል ጥብቅ የቁጥጥር እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተሰማ። ይህ እርምጃ የተወሰደው የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ከሚያዚያ 5/2018 ዓ.ም (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) ጀምሮ ሰርጡን እንደሚዘጋ ካስታወቀ በኋላ ነው።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በሰርጡ ላይ የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ የመቆጣጠርና የመገደብ ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ወደ ተግባር መግባቱ ተገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን መርከቦች በተከለከለው የሰርጡ ክልል ውስጥ ቢገኙ "እስከወዲያኛው ይሰናበታሉ" (ይደመሰሳሉ) የሚል ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ዕዙም ከኢራን ወደቦች ወደ ሰርጡ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ ለማገድ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የቴህራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በበኩሉ አሜሪካ የወሰደችው እርምጃ ዓለም አቀፍ የባህር ህግጋትን የጣሰ ነው በማለት ወቅሷል። የኢራን ወታደራዊ ኃይሎች ለአሜሪካ እርምጃ ተመጣጣኝ ምላሽ እንደሚሰጡ ዝተዋል።
በአሁኑ ወቅት አንድ የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ እና ሁለት አውዳሚዎች በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ ተሰማርተው ዝግጁነታቸውን እያረጋገጡ መሆኑ ታውቋል።
ይህ በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የተጀመረው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያና በባህር ትራንስፖርት ደህንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ
#nbc #getutemesgen #getu #hormuzstrait #usnavy #centcom #iran #trump #middleeasttension #maritimesecurity #globalnews #ኢራን #አሜሪካ #ሆርሙዝ #ወታደራዊዜና

Comments