6 months ago
"ቶተንሃም ትልቅ ክለብ አይደለም" — አንሄ ፖስቴኮግሉ
#ethiopia | የቀድሞው የቶተንሃም ሆትስፐር አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ላይ ያልተጠበቀ እና ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል። አሰልጣኙ ክለቡ "ትልቅ" ከሚባሉ የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ተርታ እንደማይመደብ በዝርዝር አስረድተዋል።
"የተግባር እና የቃል መቃረን"
ፖስቴኮግሉ ለትችታቸው ዋነኛ ምክንያት ያደረጉት የክለቡን የፋይናንስ መዋቅር እና የአሸናፊነት መንፈስ ማነስን ነው፦
* የገንዘብ አጠቃቀም፦ "ክለቡ ለዝውውር የሚያወጣውን ገንዘብ እና የደመወዝ ክፍያ ስታዩ ቶተንሃም ትልቅ ክለብ አለመሆኑን ትረዳላችሁ" ሲሉ የፋይናንስ አቅሙ ከትልልቆቹ ጋር እንደማይመጣጠን ገልጸዋል።
* ባዶ መፈክር፦ በክለቡ በየቦታው የሚታየው 'To Dare Is To Do' (መድፈር ማድረግ ነው) የሚለው መፈክር ከተግባር ጋር እንደማይገናኝ አሰልጣኙ ተናግረዋል። "ተግባራቸው ከመፈክሩ ፍጹም ተቃራኒ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ለማሸነፍ አደጋዎችን መጋፈጥ (Risk መውሰድ) ያስፈልጋል" ሲሉ ክለቡን ወቅሰዋል።
አሰልጣኙ አክለውም ቶተንሃም በወሬ እንጂ በእውነታው ከፕሪሚየር ሊጉ ታላላቅ ክለቦች አንዱ አለመሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል። ይህ አስተያየት በስፐርስ ደጋፊዎች እና በስፖርቱ ዓለም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #tottenham #spurs #postecoglou #premierleague #footballnews #todareistodo #epl #transfermarket #አውሮፓ

Comments