9 months ago
" ተጠርጣሪው ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕፃኑን በመግደል ተከራይቶ ይኖርበት በነበረው የሟች ታዳጊ አያት ግቢ በሚገኝ መፀዳጃ ቤት መጣሉን ከተያዘ በኋላ በሰጠው መረጃ አስክሬኑ ተገኝቷል " - ፖሊስ
➡️ " የአርባምንጭ ነዋሪዎችን ያስቆጣ ድርጊት የፈፀመዉ ግለሰብ በጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢዉን ፍርድ ያገኛል "
በአርባ ምንጭ ከተማ በቀን 3/3/18 ዓ/ም ናትናኤል ማይክል የተባለ በግምት የ10 ዓመት ታዳጊ ከቤት መጥፋቱን ቤተሰቦች ለፖሊስ ያሳውቃሉ።
ይህን ተከትሎ ፖሊስ ፍለጋ ይጀምራል።
ፖሊስ ከሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመሆን ክትትልና አፕሬሽን ሲያደርግ ቆይቶ ዛሬ አንድ ተጠሪጣሪ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪው ወርቁ አሰፋ ይባላል።
ግለሰቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ሴቻ ቀበሌ ዶሳ ቀጠና ፖሪቲ ስፕሪንግ ሆቴል ጀርባ ተከራይቶ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ የነበረን ታዳጊ አፍኖ በመውሰድ ከወላጆቹ ገንዘብ መጠየቁንና የሕፃኑ ወላጅ እናት የተጠየቀችውን 50 ሺህ ብር በባንክ ማስተላለፏን መረጃ ማግኘታቸውን ኮማንደር ክበበው ገልፀዋል።
ግለሰቡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ የተመረቀ እንደሆነ በሚገልፅ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ምክንያት በቅርቡ ከሚሰራበት ትምህርት ቤት መባረሩን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮማንደር ክበበው ተናግረዋል።
ይኸው ግለሰብ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕፃኑን በመግደል ተከራይቶ ይኖርበት በነበረው የሟች ታዳጊ አያት ግቢ በሚገኝ መፀዳጃ ቤት ውስጥ መጣሉን ከተያዘ በኋላ በሰጠው መረጃ አስክሬኑ መገኘቱንም አስረድተዋል።
ግለሰቡ ይህን ሕዝብን ያስቆጣ ዘግናኝ ድርጊት ከፈፀመ በኋላ በሚኒባስ ተሳፍሮ ከከተማ ለመውጣት ሲሞክር የፀጥታ ኃይሉ ከመረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በመሆን ባደረገው ክትትል በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ፉራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።
ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕዝቡን ያስቆጣ ዘግናኝ ድርጊት የፈፀመውን ግለሰብ ለሕግ በማቅረብ ፈጣንና ተገቢውን ፍርድ እንደሚያሰጥም ገልፀዋል።
ሕብረተሰቡ በትዕግስት እና በመፅናናት የምርመራና የፍርድ ውሳኔዉን እንዲጠባበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ማህበረሰቡ ፦
- መኖሪያ ቤቶችን በሚያከራይበት ወቅት፣
- የአልጋ ቤት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፣
- በቅጥርና ውሎች ወቅት ግለሰቦችን ህጋዊ የቀበሌ ነዋሪነት ወይም ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ መያዛቸውንና ትክክለኛ አድራሻቸውንና የመጡበት ምክንያት ፣ የሚሰሩበት ተቋም ወይም ድርጅትን በማጣራት እንዲሁም ህጋዊ ተያዥ መኖሩን በማረጋገጥ ማከራየትና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#tikvahethiopiafamilyhawssa
tikvahethiopia

" ያለ ስራ ስነምግባር በስራ ቦታ ባልተገባ መንገድ ሰራተኛን የደበደበ ቻይናዊን ጨምሮ በአራት ሰዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል " - የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ
➡️ " ልጁ ሕክምና ተደርጎለት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል "
በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባደረሱት ቅሬታ በፓርኩ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በውጭ ሀገራት ዜጎች አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል።
ባሳለፍነው እሁድም በፓርኩ ውስጥ በሚገኝ 'ቶዮ ሶላር' በተባለ ኩባንያ አንድ ቻይናዊ አንድን ኢትዮጵያዊ ሲደበደበዉና ልጁም መሬት ላይ ወድቆ የሚያሳይ ቪዲዮም ልከዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቪዲዮዉን ከተመለከተ በኋላ የቶዮ ሶላር ካምፓኒ ሰራተኞችንና አመራሮች እንዲሁም የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥራ አስኪያጅ ለማነጋገር ሞክሯል።
ሰራተኞች ምን አሉ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቶዮ ሶላር ካምፓኒ ሰራተኞች አግኝቶ ለማነጋገር ቢሞክርም ለደህንነታቸው ሲሉ ለጊዜዉ ያለውን ችግር ለማውራት እንዳልተመቻቸው ገልፀው በሌላ ጊዜ መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
በሌላ መልኩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቶዮ ሶላር ካምፓኒ አመራሮችን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ስልክ ባለማንሳታቸው ለጊዜው አልተሳካም።
ነገር ግን በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሰሩ ሌሎች ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " መብታችን ተረግጦ ነው እየሰራን ያለነው። የዚህ ልጅ ድብደባ በቪድዮ ወጣ እንጂ ሌሎችም ብዙ መሰል ነገር ያጋጥማቸዋል። ለሰው ኃይል ክፍል ሲከሱ ብር ይቀጧቸውና ወደ ስራ ነው የሚመልሷቸው " ብለዋል።
" አቤት የምንልበት አጥተናል ሰው እንዴት በሀገሩ እንዲህ ይደረጋል ? የምንሰራው አስራ ሁለት ሰዓት ነው። በዛ ላይ ክፍያው ልፋታችንን የሚመጥን አይደለም ለመኖር ነው የምንሰራው። እንደዛም ሆኖ ግን ክብር በሌለበት ነው የምንሰራው። ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ድብደባ፣ ስድብ ፣ ማንቋሸሽ ይደርስባቸዋል፤ የጉልበት ስራ እንደ አህያ እያሸከሙ ነው የሚያሰሩት " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይሄን ነገር መንግሥት ያውቀዋል ? ከባድ ነገር ነው እየገጠመን ያለው፤ ድምጻችንን ስሙልን " ብለዋል።
ፓርኩ ምን ምላሽ ሰጠ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አሸናፊን አግኝቶ አነጋግሯል።
አቶ ማቴዎስ ፤ " በፓርኩ በሚገኘዉ ቶዮ ሶላር ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ በሚሰራ ኢትዮጵያዊ ሞያተኛ እና የውጪ ሀገር (ቻይናዊ) ዜግነት ባለው ሱፐር ቫይዘር መካከል በስራ ቦታቸዉ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት የተስተዋለው ጠብና ድብድብ ፍፁም ከስራ መርህ ውጭ የሆነና የፓርኩን መተዳደሪያ ደንብ የሚፃረር ነው ፤ የሚወገዝም ተግባር ነው " ብለዋል።
ፓርኩ ከኢትዮጵያ ኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ በሂደቱ ውሰጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን ሁለት የውጪ ዜጎች ከስራ እንዲባረሩና #ከሀገር_እንዲወጡ እንዲሁም በካምፓኒዉ ውስጥ ያሉ በጉዳዩ ቀጥተኛ ተሳታፊ ያልሆኑ ሶስት አመራሮች ደግሞ ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው መደረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈ ፥ ካምፓኒው ጉዳዩ በቪዲዮ ከተላለፈው በዘለለ በሰራተኛውና በቅርብ አለቃው መካከል ለተስተዋለው ግጭት መነሻ የነበሩ ምክንያቶችን በመዘርዘር ሁለቱም የተጋጩበትን መንገድ ፤ ኢትዮጵያዊውም የነበረውን ጥፋቶች በመዘርዘር ከስራ እንዲባረር ወስኖ የነበረ ሲሆን ፓርኩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ስራ እንዲመለስ መወሰኑን ተናግረዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚዘዋወሩ መረጃዎች መበራከታቸውን በመግለፅ " ልጁ ሞቷል፣ አጥንቱ ተሰብሯል " የሚሉና መሰል መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
" ልጁ ሕክምና ተደርጎለት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል " ሲሉ አክለዋል።

12 months ago
" የአደጋዉን ትክክለኛ መንስኤ መራማሪ ፖሊስ አባላህ እያጣሩ ነው " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘዉ አትነት የገበያ ማዕከል ጀርባ ዛረ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።
በሕብረተሰቡና በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እሳት ማጥፊያ መኪኖች ታግዞ እሳቱ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን በሀዋሳ ከተማ ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ምክትል ዳይሬክቶረት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ዕድገት እንዳለለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" የአደጋዉን ትክክለኛ መንስኤ መራማሪ ፖሊስ አባላት እያጣሩ " ነው ያለቱ ም/ኮማንደሩ " በአደጋዉ ከዋናዉ ህንፃ ጀርባ የነበሩ ሁለት ተያያዥ ኮንተነር ሱቆች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ፤ በሕብረተሰቡና የፀጥታ ሃይሉ ርብርብ እሳቱ ወደ አትነት የገበያ ማዕከል ዋናዉ ሕንፃና ወደ ቅዱስ ገበርኤል ትምህርት ቤት እንዳይዛመት ተደርጎ በቁጥጥር ስር ዉሏል " ብለዋል።

Comments