3 months ago
የኔ ሄልዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሴቶችን የጤና አገልግሎት እና የመድኃኒት አቅርቦት ስርአትን ለማቃለል በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ የጀመረው "የኔ ሄልዝ" ፣ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አደረገ።
የድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ ቅድስት ተስፋዬ እንደገለጹት፣ "የኔ ሄልዝ" ባለፉት አራት ዓመታት በሴቶች ጤና እና በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል። ድርጅቱ በተለይ በሞባይል መተግበሪያው (App) አማካኝነት ለሴቶች ሦስት ዋና ዋና አገልግሎቶችን ይሰጣል፡
* የጤና መረጃ፡ ስለ እርግዝና፣ ስለ የወር አበባ ዑደትና ስለ ተለያዩ መድኃኒቶች ግንዛቤ የሚሰጡ መረጃዎች።
* የቴሌ ሄልዝ (Tele-Health) አገልግሎት፡ ታካሚዎች በቪዲዮ፣ በቻት ወይም በስልክ ከሐኪሞችና ከፋርማሲስቶች ጋር በቀጥታ በመገናኘት ምክክር የሚያደርጉበትና መድኃኒት የሚታዘዝበት ሥርዓት።
* የኦንላይን ፋርማሲ፡ የታዘዘላቸውን መድኃኒት ወይም የውጭ አገር የሕክምና ትዕዛዝ (Prescription) በመተግበሪያው ላይ በመጫን መድኃኒቱን ባሉበት ቦታ ድረስ እንዲመጣላቸው የሚያደርግ አገልግሎት።
ድርጅቱ አሁን ላይ አገልግሎቱን በማስፋት ከባንኮች ጋር በመተባበር ለፋርማሲዎችና ለጤና ተቋማት የብድር አቅርቦት ማመቻቸት መጀመሩን ገልጿል። ይህ አሰራር ፋርማሲዎች የገንዘብ እጥረት ሳይገጥማቸው መድኃኒቶችን በቋሚነት እንዲያቀርቡና ህብረተሰቡ የመድኃኒት እጥረት እንዳይገጥመው ለማድረግ ያለመ ነው።
በተጨማሪም "የኔ ሄልዝ" ከ60 በላይ ከሚሆኑ አምራቾች፣ አስመጪዎችና የጤና ተቋማት ጋር የጅምላ ግብይት ትስስር (Online Wholesale Platform) መፍጠሩ ተጠቁሟል።
በአገሪቱ ያለውን ዝቅተኛ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤ (Digital Literacy) ለመቅረፍ፣ ድርጅቱ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለተማሪዎችና ለተጠቃሚዎች መተግበሪያውን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ስልጠናዎችን እየሰጠ ሲሆን መተግበሪያውም ተጠቃሚዎች እንዳይሰላቹ በቀላልና ምቹ በሆነ መንገድ (User Friendly) እንዲዘጋጅ ተደርጓል።
"የኔ ሄልዝ" ዛሬ ባካሄደው ዓመታዊ የውይይት መድረክ ላይ ከመንግሥት አካላት (ከኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለሥልጣን - EFDA) እና ከኢትዮጵያ መድኃኒት ማህበር ጋር በመሆን የኦንላይን መድኃኒት ግብይትና አቅርቦት ሕጋዊ ማዕቀፎች እንዲጠናከሩ ውይይቶችን አድርጓል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የኔ_ሄልዝ #የሴቶች_ጤና #ቴክኖሎጂ #ጤና #ኢትዮጵያ #yenehealth #telehealth #digitalhealth