5 months ago
✈️ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ኩራት እና የአህጉሪቱ የትስስር ምሰሶ ነው" — ፕሮፌሰር ጆሴፍ ሜንሳህ
#ethiopia | የዮርክ ዩኒቨርሲቲ ምሁር የሆኑት ጋናዊው ፕሮፌሰር ጆሴፍ ሜንሳህ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከራሷና ከቀሪው ዓለም ጋር በማስተሳሰር ረገድ የሚጫወተው ሚና እጅግ የሚደነቅና "የአፍሪካ ኩራት" መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ነው አሉ።
ፕሮፌሰሩ ከኢቲቪ "አዲስ ዳያሎግ" ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🌍 የአየር መንገዱ ስትራቴጂካዊ መስፋፋት
አየር መንገዱ በአፍሪካ ውስጥ በሎሜ፣ ሉሳካ እና ሊሎንግዌ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ወደ ፊሊፒንስ እና ጄኔቫ አዳዲስ መዳረሻዎችን በመክፈት የጀመረውን ስትራቴጂካዊ ጉዞ አጠናክሮ መቀጠሉን ምሁሩ አድንቀዋል
🏗️ የቢሾፍቱ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት
በ12.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው አዲሱ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለኢኮኖሚው ትልቅ አቅም እንደሚሆን ፕሮፌሰር ጆሴፍ ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት፦
* ለአፍሪካ ትስስር አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ይከፍታል።
* ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
* ቦታን እና ጊዜን በማቀራረብ ረገድ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።
📈 ማክሮ ኢኮኖሚ እና የወጣቱ አቅም
ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ "የመፍጠር እና የማደስ" ባህሪ እንዳለው የጠቆሙት ምሁሩ፣ መንግሥት ችግር ሲፈጠር ብቻ ምላሽ ከመስጠት ወጥቶ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቁ ዕቅዶች ላይ ማተኮሩን አድንቀዋል። አክለውም፣ ኢትዮጵያ ያላት ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ለቀጣይ ሁለት አሥርት ዓመታት ትልቁ ሀብቷ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንን አቅም ለመጠቀም በቂ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችው ይህ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግራት ፕሮፌሰር ጆሴፍ ሜንሳህ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopianairlines #africanpride #economicreform #aviationnews #ethiopia #professorjosephmensah #addisdialogue #africaunion #strategicplanning

Comments