18 days ago
"መታሰር አልፈልግም" ቦርጃ
#ethiopia | የአሜሪካ አስተዳደር እና የፖለቲካ ስርአት በመቃወም የሚታወቀው ስፔናዊው ተጫዋች ቦርጃ ኢግሌሲያስ ዋንጫውን ካነሳን ለፕሬዝዳንቱ ሰላምታ አልሰጥም ሲል በአንድ ቃለ መጠየቅ ተናግሮ ነበር።
ሆኖም ትላንት ምሽች ይህንን ቃሉ መተግበር አልቻለም።
የስፔኑ አጥቂ ቦርጃ ኢግሌሲያስ በዓለም ዋንጫው የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ለዶናልድ ትራምፕ ሰላምታ የሰጠበትን ምክንያት አስረድቷል።
ሁሉም ሰው በጣም ደስተኛ በሆነበት ሰአት ለፕሬዝዳንቱ ሰላምታዬን መስጠት እና ተቃውሞዬን በሌላ መድረክ ብግልጽ ይሻላል በሚል ነው ያደረኩት ብሏል።
ቦታው አወዛጋቢ እና አነጋጋሪ የሆኑ ጉዳዮች የምንፈጥርበት ባለመሆኑ ነው ሰላምታዬን ለፕሬዝዳንቱ የሰጠሁት ሲል ተናግሯል።
በተለያዩ ጉዳዮች ያለኝን አቋምና አመለካከት ብዙዎች በደንብ ያውቁታል ሲልም አክሏል።
ተጫዋቹ ይህንን ውሳኔ የወሰነው ሰላምታውን ባለመቀበል ችግር ውስጥ ላለመግባት እና እስር ቤት ላለመውረድ በሚል እንደሆነ አስታውቋል።
በፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ተቃውሞውን የሚገልጸው ቦርጃ ኢግሌሲያስ ከዚህ ቀደም ለፍልስጤም ተቃዋሚዎች ድጋፍ መስጠቱን እንዲሁም የ"Black Lives Matter" ንቅናቄን ለመደገፍ ጥፍሮቹን በጥቁር ቀለም መቀባቱን ተከትሎ ማስፈራርያ ደርሶበት ነበር።
ብዙ ነገሮችን ማድረግ ብፈልግና ሰዎች ተጽኖ ፈጣሪ እንደሆንኩ ቢገምቱም አንዳንድ ነገሮችን ከመጋፈጥ መቆጠብ ያስፈልጋል ብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #spainstrikerborjaiglesias #shakedonaldtrumphand #worldcupfinal

Comments