1 month ago
የኮሪደር ልማት ከከተማ ወደ ገጠር፡ የፍትሐዊነት እና የዜጎች ክብር አዲሱ ምዕራፍ
************************
ኢትዮጵያን የሚመጥን ዘመናዊ ገጽታን ለመገንባት እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ መንግሥት በአዲስ አበባ የጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ዛሬ ላይ የሀገራችን ከተሞች ዋነኛ መገለጫና አዲስ የልማት ባህል ሆኖ ተሻግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከኮሪደር ልማቱ በፊት የነበራትን ገጽታ እና የመጀመሪያው ዙር ልማት ከተጠናቀቀ በኋላ ያገኘችውን አስደናቂ ውበትና ምቾት እንደ አብነት በመውሰድ፣ በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የኮሪደር ልማት በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።
ይህ የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ከመሆኑም በላይ፣ ሁሉንም ዜጋ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ ልማትን ለሕዝብ ለማቅረብ ያለመ በመሆኑ ለሌሎች ሀገራት ጭምር አርዓያና ምሳሌ ሊሆን በሚችል መልኩ እየተተገበረ ይገኛል።
ሆኖም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የሚኖረው በገጠር አካባቢዎች በመሆኑ፣ የዜጎችን ሕይወት በተሟላ መልኩ ለመቀየር እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ዕውን ለማድረግ በከተሞች ላይ ብቻ የሚሠራው የኮሪደር ልማት በቂ ሊሆን አይችልም።
በከተሞች የታየው አመርቂ እና ተጨባጭ ውጤት በገጠርም መደገም አለበት ከሚል ጽኑ ሀገራዊ ራዕይ በመነሳት፣ ልማቱ አድማሱን በማስፋት የገጠሩን ማኅበረሰብ አኗኗር ወደሚያሻሽል የገጠር ኮሪደር ልማት ተሸጋግሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህም የገጠር ኮሪደር ልማት እና ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2017 ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
የገጠር ኮሪደር ልማት ዋነኛ ግቡም የተስተካከለ የኑሮ ዘይቤን እና ዘመናዊ ከተሜነትን ወደ ገጠር ማምጣት ሲሆን፣ የሚገነቡት ሞዴል መንደሮችም ቀላል ወጪ የሚጠይቁ እና በአካባቢው በሚገኙ ሀገር በቀል ግብዓቶች የሚገነቡ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።
ይህም አርሶ አደሩ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ጤናማ፣ ፅዱ እና ክብሩን የጠበቀ ዘመናዊ ሕይወት እንዲመራ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
ልማቱ በውጤት ደረጃ የኅብረተሰብ ሽግግርን የሚያመጣ እና የመሠረተ ልማት ተጠቃሚነትን በፍትሐዊነት የሚያረጋግጥ ነው።
በሌላ በኩል ከለውጡ በፊት የሀገራችን የኢኮኖሚ ዋነኛ ምንጭ የሆነው የገጠሩ አካባቢ ተገቢውን ትኩረት አጥቶ በመቆየቱ ምክንያት፣ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ወደ ከተሞች የሚሰደደው የወጣት ቁጥር ከፍተኛ ነበር።
የገጠር ኮሪደር ልማት ግን፣ የተመጣጠነ የሀገር ዕድገትን በሁሉም አካባቢ በማምጣት ይህንን ፍልሰት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
ወጣቶችም የተሻለ ሕይወት ፍለጋ መሰደድ ሳይጠበቅባቸው በሚኖሩበት አካባቢ ተረጋግተው በተለያዩ የልማት ዘርፎች እንዲሰማሩ እንዲሁም በግብርና ውጤቶች ላይ እሴት በመጨመር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፤ በመፍጠርም ላይ ይገኛል።
ይህ ሥራ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ፋይዳ ያለው ዘርፈ-ብዙ ስትራቴጂ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆን እና ዘመናዊ ስልተ-ምርትን እንዲከተል በማድረግ አዲስ የአኗኗር ባህል በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ይተክላል።
ይህም በሀገር ደረጃ የምግብ ሉዓላዊነትን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት እና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር የሚያስችል ምቹ ዐውድ እየፈጠረ ይገኛል።
የኮሪደር ልማቱ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ገጽታና አኗኗር የሚቀይር ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ሲሆን፣ በዚህም በገጠር የሀገሪቱ አካባቢዎች ዘመናዊ አኗኗርን በመፍጠር፣ የአርሶ አደሩን ሕይወት በማሻሻል እና የከተማና የገጠርን የኑሮ ልዩነት በማጥበብ ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ መሠረት እየጣለ ይገኛል።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #ebc #corriderdevelopment #ruralcorriderdevelopment #ruraltransformation

Comments