7 months ago
🎖️ የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል (CISM) ፕሬዘዳንት በታሪካዊው መቻል ስፖርት ክለብ! 🇪🇹⚽
"መቻል ስፖርት ክለብ ባለው አደረጃጀት ተደንቀናል፤ በቀጣይም አብረን እንሰራለን" - ኮሎኔል ኒልቶን ጎሜዝ
#ethiopia | የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል (CISM) ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ኒልቶን ጎሜዝ፣ የአፍሪካ ወታደራዊ ስፖርት (OSMA) ፕሬዝዳንት ሜጄር ጄኔራል መኪያኖ አብዱላሂ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ስፖርት ቀዳሚ የሆነውን መቻል ስፖርት ክለብን ጎብኝተዋል።
የጉብኝቱ ድባብና ዓላማ፡
✅ አቀባበል፡ አመራሮቹ ክለቡ ጋር ሲደርሱ በመከላከያ ክብር ዘብ እና ማርችንግ ባንድ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
✅ ዓላማ፡ የመቻል ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰይፉ ጌታሁን እንደገለጹት፤ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አቅም በማሳየት በቀጣይ ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየሞችን እና ጉባኤዎችን እንድታዘጋጅ ለማመቻቸት ያለመ ነው።
✅ አዲስ እድል፡ የመቻል ስራ አስፈጻሚ ብ/ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን፤ ጉብኝቱ ክለቡ በቀጣይ በቱርክ (ግማሽ ማራቶን) እና በግሪክ (አገር አቆራጭ) በሚደረጉ ውድድሮች ለመሳተፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል።
አመራሮቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝዬምን እና የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝዬምን በመጎብኘት የኢትዮጵያን ታሪክ አድንቀዋል።
ዘጋቢ፡ በላቸው ክንዴ
ፎቶ፡ አበረ አየነው
#mechalsportclub #cism #osma #militarysports #ethiopia #sportsdiplomacy

Comments