4 months ago
ትራምፕ በኢራኗ ኻርግ ደሴት ላይ አይናቸውን ጥለዋል
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የኢራንን የነዳጅ ዘይት ሀብት ለመቀራመትና ስልታዊ ጠቀሜታ ያላትን የኻርግ ደሴትን በቀላሉ ልትቆጣጠር እንደምትችል ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ ከፋይናንሺያል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢራንን የነዳጅ ምርት የመረከብ ፍላጎት እንዳላቸው በግልጽ ተናግረዋል።
ትራምፕ አሜሪካ ኻርግ ደሴትን ለመቆጣጠር የሚያግዳት አንዳችም የኢራን መከላከያ እንደሌለ ገልጸው፣ "በቀላሉ ልንወስዳት እንችላለን" ብለዋል።
"እውነቱን ለመናገር ከኢራን የነዳጅ ዘይት መውሰድ እፈልጋለሁ" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ይህንን እርምጃ የሚቃወሙ ወገኖችን "የማይረቡ" ሲሉ ነቅፈዋል።
ከነዳጅ በተጨማሪ አሜሪካ በኢራን የሚገኘውን የዩራኒየም ክምችት ለማውጣት እያሰበች መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል
ፕሬዚዳንቱ ወታደራዊ እርምጃውን እንደ አማራጭ ቢያነሱም፣ ጉዳዩ "በፍጥነት እና ፍትሃዊ" በሆነ የሰላም ስምምነት እንዲቋጭ እንደሚፈልጉም አልሸሸጉም።
ይህ ንግግር የወጣው 3,500 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች በመካከለኛው ምስራቅ መድረሳቸው በታወቀበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል። ኻርግ ደሴት ለኢራን የነዳጅ ኤክስፖርት ወሳኝ የባህር በር መሆኗ ይታወቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #trump #iran #khargisland #middleeast #oilpolitics #globalnews #usa #geopolitics2025

Comments