2 months ago
በኢራን ተራራማ ምድር የተካሄደው አስገራሚው ኦፕሬሽን !
"አሜሪካ የአየር ኃይል መኮንኗን ከኢራን ለማስለቀቅ ያከናወነችው ኦፕሬሽን እንዴት ተካሄደ?"
የኔታ ሚዲያ
የአለምን ትኩረት በሳበውና በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በነበረው የኢራን እና አሜሪካ ግጭት ውስጥ ሌላ አዲስ አስገራሚ ክስተት ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳስታወቁት በኢራን ምድር የጦር አውሮፕላናቸው ተመትቶባቸው ተሰውረው የነበሩት ሁለተኛው የአየር ኃይል መኮንን በልዩ ኮማንዶ ኦፕሬሽን በሰላም ተርፈዋል።
ባለፈው አርብ እለት የአሜሪካው ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን F-15E ስትራይክ ኢግል (Strike Eagle) በደቡባዊ ኢራን ላይ ተመትቶ ወደቀ። አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሁለት መኮንኖች በፓራሹት ዘልለው ቢወጡም አብራሪው (Pilot) ወዲያውኑ ሲገኝ የጦር መሳሪያ ስርአት መኮንኑ (Weapons Systems Officer) ግን በኢራን አስቸጋሪ ተራራማ ስፍራዎች ውስጥ ተሰውሮ ለሁለት ቀናት ቆይቷል።
የ7 ሰዓታት የሞት እና የሽረት ትግል!
ፕሬዝዳንት ትራምፕ "በጣም የተከበሩ ኮሎኔል" ሲሉ የጠሯቸው ይህ መኮንን በኢራን ወታደሮች እየታደኑ ለሁለት ቀናት በተራራማው የኮጊሉዬህ እና ቦየር-አህመድ ግዛት ውስጥ ለመደበቅ ተገደው ነበር።
ኢራን መኮንኑን በቁጥጥር ስር አውላ ለፖለቲካዊ መጠቀሚያ (የጦር ምርኮኛ) ለማድረግ ከፍተኛ ፍለጋ ብታደርግም አሜሪካ ግን በመኮንኑ ላይ የተገጠመውን ዘመናዊ መከታተያ በመጠቀም በደቂቃ ልዩነት እንቅስቃሴውን ስትከታተል ነበረ።
ብቸኛ አልነበረም! ያሉት ትራምፕ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአየር ኃይል አባላት እና ዘመናዊ ጄቶች መኮንኑን ለማዳን በኢራን ሰማይ ላይ ለ7 ሰዓታት ያህል ሲያንዣብቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም በሁለተኛው ዙር ጥቃት በጠራራ ፀሐይ በተካሄደ ኦፕሬሽን መኮንኑን ከኢራን ምድር ነጥቀው አውጥተውታል።
ኦፕሬሽኑ ያለ መስዋዕትነት አላለፈም የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) እንደገለጸው በአሜሪካ የነፍስ አድኑ ዘመቻ ወቅት ሁለት የሲ-130 (C-130) የጭነት አውሮፕላኖች እና ሁለት ብላክ ሃውክ ሄሊኮፕተሮች ተመትተዋል።
አሜሪካ በበኩሏ አውሮፕላኖቹ በጠላት እጅ እንዳይወድቁ በሚል ራሷ እንዳፈነዳቻቸው ፍንጭ ሰጥታለች።
ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት የካቲት 28 ጀምሮ 13 የአሜሪካ ወታደሮች ተገድለዋል ከ300 በላይ ቆስለዋል። ነገር ግን እስካሁን በኢራን እጅ የወደቀ አንድም የአሜሪካ ወታደር የለም።
በዚሁ ኦፕሬሽን ወቅት በኢራን ምድር በተሰነዘሩ ጥቃቶች 9 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ምሽት ላይ በኋይት ሃውስ ከጦር አዛዦች ጋር በመሆን ስለ ኦፕሬሽኑ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች የኔታ ሚዲያን ይከታተሉ!
#us #iran #trump #militaryoperation #yenetamedia #ethiopia #breakingnews

"ኢራን በሀገራችን ጦርነት እያካሄደች ነው!"
የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር
#ethiopia | የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሰላም ከአል አረቢያ ጋር ባደረጉት ታሪካዊ ቃለ ምልልስ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሊባኖስ ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ በመግባት የሄዝቦላህን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቀጥታ እየመራ መሆኑን በይፋ አጋለጡ።
የኢራን ቀጥተኛ እጅ፦ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባላት በሐሰተኛ ፓስፖርት በሕገ-ወጥ መንገድ ሊባኖስ በመግባት ጦርነቱን እያቀናጁ እንደሚገኙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በቆጵሮስ በሚገኘው የብሪታንያ ጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት በሊባኖስ በሚገኙ የኢራን መኮንኖች መሪነት የተቀነባበረ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የሊባኖስ መንግስት ማንኛውም የኢራን አብዮታዊ ዘብ እንቅስቃሴ በሀገሪቱ እንዳይኖር ያገደ ሲሆን፣ ሄዝቦላህም ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን እንዲያቆምና ትጥቁን ለመንግስት እንዲያስረክብ ጥሪ አቅርቧል።
ይህ ጦርነት የሊባኖስ ፍላጎት ሳይሆን የኢራኑን መሪ አሊ ካሜኒን ግድያ ለመበቀል በሊባኖስ ላይ የተጫነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰላም በዝርዝር አስረድተዋል።
ይህ የሊባኖስ መንግስት ቁርጠኝነትና የሄዝቦላህ ትጥቅ የመፍታት ጥሪ፣ በቀጠናው ለሚጠበቀው ሰላም ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ተነግሯል።
#getu #lebanon #iran #hezbollah #middleeastconflict #nawafsalam #breakingnews #internationalpolitics #militaryoperation #ሊባኖስ #ኢራን #ሄዝቦላህ #ሰበርዜና #መካከለኛውምስራቅ #ጌጡተመስገን #getutemesgen