4 months ago
🏆 "ብቻዬን አይደለሁም... እብድም አይደለሁም!!" 🚑
#ethiopia | የጠብታ አምቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ በዳቦስ የ2026 የሽዋብ ፋውንዴሽን (Schwab Foundation Award) ሽልማትን ካሸነፉ በኋላ ያሰሙት ልብ የሚነካ ንግግር!
ማክሰኞ ጥር 12/ 2018 ዓ.ም በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ ቆመው ያደረጉት ንግግር የብዙዎችን ልብ ነክቷል።
ጉዞው ምን ይመስል ነበር?
ህልማቸውን ለማሳካት አንድ ቤታቸውን ሸጠው አምቡላንስ ሲያመጡ፤ አብረዋቸው ይሰሩ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች "ሰውየው እብደት ጀምሮታል" ብለው ርቀዋቸው ነበር።
"በሰው ተከብቤ የምውል ሰው በሰው ድርቅ ተመታሁ... ስልኬን የሚያቃጭሉት ባለቤቴና እናቴ ብቻ ነበሩ" ይላሉ አቶ ክብረት።
ነገር ግን ያኔ "እብድ ነው" ብለው የሸሹት ሰዎች፤ በዚሁ በአቶ ክብረት አምቡላንስ እና ቬንቲሌተር የታካሚ ህይወት ሲተርፍ እውነቱን ተረድተው ይቅርታ ጠይቀዋል።
ዛሬ ያ ሁሉ ተጋድሎ ፍሬ አፍርቶ በዓለም አቀፍ መድረክ ሲሸለሙ፤ ለዓለም እንዲህ ሲሉ አወጁ፦
"ይህ ሽልማት ያረጋገጠልኝ ነገር ቢኖር... ብቻዬን እንዳልሆንኩ እና እብድም እንዳልሆንኩ ነው!"
ቀጣይ ጉዞ ወደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (ቦስተን)! ✈️🇺🇸
ይህ ድል የኢትዮጵያም ድል ነው! እንኳን ደስ አለዎት! 🇪🇹👏
#kibretabebe #tebitaambulance #schwabfoundation2026 #davos #socialentrepreneur #ethiopia #inspiration #harvard

የ"ጠብታ አምቡላንስ" መስራች በዳቮስ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፉ! 🏆🚑
"ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ - አቶ ክብረት አበበ"
#ethiopia | በስዊዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum) ላይ፤ የጠብታ አምቡላንስ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ክብረት አበበ፤ የ2026 የ"ሽዋብ ፋውንዴሽን" (Schwab Foundation) ዓለም አቀፍ ተሸላሚ በመሆን የኢትዮጵያን ስም አስጠሩ።
ለምን ተሸለሙ?
አቶ ክብረት ይህንን ክብር ያገኙት ማህበራዊ ችግሮችን በሥራ ፈጠራ ሀሳቦች በመፍታት (Social Innovation) ላሳዩት ውጤታማነት ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ከተመረጡት 21 ዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ለመሆን በቅተዋል።
ልዩ አጋጣሚ:
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል አቶ ክብረትን ባደነቁበት ንግግራቸው፤ "ይህ ሽልማት በተሰጠበት ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 'የሥራ ፈጠራ ህግን' ማፅደቁ ልዩ አጋጣሚ ነው" ብለዋል።
ይህ ድል የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችሉ ህያው ማሳያ ነው!
እንኳን ደስ አለዎት! 👏👏
#ethiopia #davos2026 #worldeconomicforum #kibretabebe #tebitaambulance #socialinnovation #schwabfoundation #pride