5 months ago
2 ሺህ የንግሥት ጉንዳኖችን ወደ ቻይና ሊያሰግር የነበረው ግለሰብ በናይሮቢ ተያዘ
#ethiopia | በኬንያ ናይሮቢ ጆሞ ኬኒያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከ2 ሺህ በላይ የንግሥት ጉንዳኖችን በሻንጣው ደብቆ ለማውጣት የሞከረ ቻይናዊ በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ዛንግ ኬቁን የተባለው የ27 ዓመት ወጣት፣ እነዚህን በርካታ ቁጥር ያላቸው የንግሥት ጉንዳኖች በሻንጣው ውስጥ በድብቅ አሽጎ ከኬንያ ሊወጣ ሲል ነው በበረራ መቆጣጠሪያ ፍተሻ ላይ የተያዘው።
ተከሳሹ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸመ እስካሁን የሰጠው ምላሽ ባይኖርም፣ የኬንያ ፖሊስ መርማሪዎች ግን ግለሰቡ በአገሪቱ ውስጥ ካለ ሰፊ የጉንዳን ስርቆት መረብ (Network) ጋር ግንኙነት እንዳለው ለፍርድ ቤት አስረድተዋል።
ጉዳዩ ያልተለመደና ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፣ የምርመራው ሂደትም እነዚህ የንግሥት ጉንዳኖች ለምን ዓላማ ሊውሉ እንደታሰበ ለማወቅ ትኩረት አድርጓል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #kenya #nairobi #china #news #environment #jomokenyattaairport #wildlifetrafficking

Comments