2 months ago
በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ የተቀሰቀሰው ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና የኢራን ይፋዊ ምላሽ
********************
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ላለፉት ጊዜያት ሲብላላ የቆየው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ውጥረት አሁን ላይ ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ ይገኛል።
የሁለቱ ሀገራት እሰጥ አገባ በተለይም ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ባለው የሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ ያጠነጠነ ሲሆን፣ አሁን ላይ ቀጠናው የኃያላን የጦርነትና የዲፕሎማሲ ፍጥጫ ማዕከል ሆኗል።
ይህ አደገኛ የቃላትና የተግባር ጦርነት ዳግም ሊያገረሽ የቻለው፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥን በቅርቡ "የአሜሪካ ግዛት" አድርገው ለማወጅ ማቀዳቸውን በይፋ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።
ይህንን የአሜሪካን ያልተጠበቀ የባለቤትነት ጥያቄና ዛቻ ተከትሎ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፈጣንና ጠንካራ ምላሽ በመስጠት አቋሙን አንጸባርቋል።
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ካዜም ገርባባዲ በሰጡት መግለጫ፣ ይህ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ የባህር ሰርጥ በባዶ ዛቻ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ የትዊተር መልእክት ብቻ በቀላሉ ሊወሰድ እንደማይችል በአጽንኦት አሳስበዋል።
አክለውም ይህ ወሳኝ የውሃ መንገድ ሙሉ በሙሉ በኢራን መንግስት ህጋዊ ቁጥጥር ስር መሆኑን በማስታወቅ፣ አሜሪካ በቀጠናው ያላትን ተጽዕኖ አጥብቀው ተቃውመዋል።
ከዚህም ባሻገር የኢራን መንግስት በወሰደው እርምጃ ወደ ኋላ እንደማይል በመግለፅ፣ አሜሪካ በይፋ ሽንፈቷን አምና ሳትቀበል እንዲሁም የታጠቁ ወታደራዊ ኃይሎቿን ከቀጠናው ሙሉ በሙሉ ሳታስወጣ በሰርጡ ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ በምንም ተአምር እንደማይነሳ አስጠንቅቋል።
በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ሀገራት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ የባህር መንገድ ላይ የኃይል የበላይነታቸውን ለማሳየት እርስ በእርስ ተደጋጋሚ የባህር ላይ እገዳዎችን እያካሄዱ ሲሆን፣ ይህ አሳሳቢ ሁኔታም ዓለም አቀፉን የንግድና የደህንነት እንቅስቃሴ በእጅጉ ስጋት ውስጥ ጥሎት ይገኛል።
በሰለሞን ገዳ
#straitofhormuz #iranusrelations #geopolitics #middleeasttensions #maritimesecurity

Comments