14 days ago
የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ያስገኘው ትሩፋት
*****************
በቅርቡ በኢትዮጵያ የተተገበሩት የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥረዋል።
ይህ መነቃቃት ለሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ የግብዓት አቅርቦት ዋነኛ የጀርባ አጥንት እየሆነ መጥቷል።
ዘርፉ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብዓት ጥገኝነት በመስበር ለግንባታ የሚያስፈልጉ ቁልፍ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመሩ፣ የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገቱን እያፋጠነው ይገኛል።
ከ7 ዓመታት በፊት ፋብሪካዎች በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ በኃይል መቆራረጥ እና በግብዓት እጥረት ምክንያት በአማካይ የማምረት አቅማቸውን 47 በመቶ ብቻ ይጠቀሙ ነበር።
ሆኖም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመንግሥት በተወሰዱ የማሻሻያ እርምዎች ተዘግተው የነበሩ 993 ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ተመልሰዋል። በተለይ የማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ፈጣን መዋቅራዊ ለውጥ ማስመዝገብ ችለዋል።
በተተገበሩት ማሻሻያዎች በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪው ዘርፍ የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ የዘርፉ ዕድገትም ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ከፍ ብሏል።
በጥቅሉ የኢንዱስትሪው ዘርፍ መነቃቃት ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ካበረከታቸው አስተዋጽኦዎች ዋነኛው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉ ነው።
ለዚህ ማሳያ የሚሆኑት የሀገራችንን የሴራሚክ ፍላጎት 70 በመቶ መሸፈን የሚችለው ግዙፉ የባጃይ (ቱለፋ) ሴራሚክስ እና የሀገራችንን 50 በመቶ የሲሚንቶ ፍላጎት የሚያሟላው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ከውጭ ለሚገቡ የግንባታ ግብዓቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይወጣ የነበረ ሲሆን፣ ለአብነትም ለሴራሚክ ግዢ ብቻ ከ74 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ይባክን ነበር።
አሁን በተተገበረው የተኪ ምርት ስትራቴጂ፣ በተያዘው በጀት ዓመት 9 ወራት ብቻ 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል።
በሌላ በኩል ቀደም ሲል የፋይናንስ ሥርዓቱ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ያደላ የነበረ በመሆኑ፣ ለግሉ ዘርፍ ይደርስ የነበረው የብድር መጠን 56.3 በመቶ ብቻ ነበር።
ሆኖም ተግባራዊ በተደረገ ታሪካዊ የብድር ሽግሽግ አስገዳጅ የሆነውን የ27 በመቶ የቦንድ ግዢ በማስቀረት ጭምር ለግል ዘርፉ የሚሰጠው የብድር ድርሻ ወደ 77 በመቶ ከፍ ተደርጓል።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከነበረበት የግብዓት ጥገኝነት አዙሪት ወጥቶ የውጭ ምንዛሬን ወደሚያድን እና የግል ዘርፉን ዋነኛ ሞተር ወዳደረገ የግብዓት ሉዓላዊነት ተሸጋግሯል።
በኢኮኖሚ ማሻሻያው የመጣው ይህ መነቃቃት ሀገራችን በኢንዱስትሪ ብልጽግና ጎዳና ላይ የማይቀለበስ ታሪካዊ እርምጃ መጀመሯን የሚያረጋግጥ እና ለቀጣይ ጠንካራ ሀገራዊ የዕድገት ጉዞ ፅኑ መሠረት የጣለ ነው።
#ethiopia #economicreform #industrialawakening #manufacturing #constructionindustry #importsubstitution #inputsovereignty

Comments