6 months ago
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጽሐፍት ስጦታ አበረከቱ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይንን በኤምባሲው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሃሪ ትሩማንን ታሪክና ስራዎች የሚዘክሩ መጽሐፍትን ለዩኒቨርሲቲው በስጦታ አበርክተዋል።
ይህ ስጦታ በዩኒቨርሲቲውና በአሜሪካ መካከል ያለውንና እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ በፕሬዝዳንት ትሩማን ዘመን የተጀመረውን የቆየ አጋርነት እውቅና ለመስጠት የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ቤተ-መጽሐፍቱን በፕሬዝዳንት ሃሪ ትሩማን ስም ለመሰየም ለወሰነው ውሳኔም አምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።
አምባሳደር ማሳንጋ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበት 70ኛው ዓመት እና ከዩኒቨርሲቲው ምስረታ ቀድሞ የተቋቋመውና ለዘመናዊ ሕክምና መሰረት የሆነው የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት በዓል በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ethiopia #gondaruniversity #us_ethiopia #education #history #harrytruman #partnership #gondar

Comments