2 months ago
የምሕረትና የእዝነት ዝናብ በፈሰሰበት ታላቅ ዕለት፤ በሚሊዮን የሚጠጉ ሙዕሚኖች በአረፋት ተራራ ላይ በአላህ ፊት ቆሙ
*****************************
የዘንድሮው የ1447ኛው ዓመታዊ የሐጅ ጉዞ ከዓለም ማዕዘናት የተሰባሰቡ በሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊም ምዕመናን በምዕራባዊ ሳዑዲ አረቢያ ወደሚገኛው ታሪካዊው የአረፋት ተራራ በመጓዝ የጸሎት ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል።
ለስድስት ቀናት የሚቆየው ይህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት፣ የእስልምና እምነትን መሠረታዊ ፅንሰ-ሐሳቦች ለማመልከትና የነቢዩ ኢብራሂምን (ረ.ወ) እንዲሁም የቤተሰባቸውን ታሪካዊ ፈተናዎች በማስታወስ የሚከናወን ነው።
ምዕመናኑ በአሁኑ ወቅት በአረፋት ተራራ ላይ ዱዓ እያደረጉና አጠር ያሉ የሰዓት ሰላቶችን ይሰግዳሉ። ፀሐይ ስትጠልቅ ደግሞ የአላህን ስም እያወሱ ወደ ሙዝዳሊፋ በመጓዝ የሌሊት ጸሎታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፣ እዚያው በባዶ መሬት ላይ እስከሚቀጥለው ቀን ንጋት ድረስ በታላቅ ትሕትና ያድራሉ።
ጉዞው በአረፋት መቆም፣ በሙዝደሊፋ ማደር፣ በሚና የሰይጣን ሥራዎችን የሚቃወሙበትን የጠጠር ውርወራ ማከናወን እና በመካ በሚገኘው ታላቁ መስጊድ የካዕባ የስንብት ጠዋፍ ማድረግን ያጠቃልላል።
ኢንቲሃድ አብራር
#hajj2026 #arafat #makkah #islam #faithjourney #muslimummah

Comments