2 months ago
ጋናዊው ወጣት ተጨዋች ዶምኒክ ፍሪምፖንግ በታጣቂዎች ጥቃት ተገደለ
#ethiopia | በጋና እግር ኳስ ሊግ ታሪክ እጅግ አሰቃቂ የተባለ ጥቃት በቤሬኩም ቼልሲ ክለብ ላይ ደርሷል። የክለቡ ተስፈኛ ተጨዋች የሆነው የ20 ዓመቱ ዶምኒክ ፍሪምፖንግ በታጠቁ ዘራፊዎች በተከፈተ ጥቃት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።
ክለቡ ቤሬኩም ቼልሲ የሊግ ጨዋታውን አከናውኖ በባስ በመመለስ ላይ እያለ፣ ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ዘራፊዎች ተሽከርካሪውን አስቁመው ጥቃት ከፍተዋል።
ወጣቱ ተጨዋች ዶምኒክ ፍሪምፖንግ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት የጥይት ጉዳት ህይወቱ ወዲያውኑ አልፏል።
በጥቃቱ ሳቢያ በርካታ የቡድኑ ተጨዋቾችና የቴክኒክ አባላት ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ አንዳንድ የቡድኑ አባላት ደግሞ ያሉበት ደብዛ መጥፋቱ ተነግሯል።
የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን (GFA) ባወጣው መግለጫ በድርጊቱ እጅግ ማዘኑን ገልጾ፣ ለተጨዋቹ ቤተሰቦችና ለክለቡ ደጋፊዎች መጽናናትን ተመኝቷል። ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ #getutemesgen #getu #tikvahsport #ghana #berekumchelsea #dominicfrimpong #gfa #footballnews #africasports #ghanapremierleague #ጋና #እግርኳስ #አሳዛኝዜና

Comments