7 months ago
❤️ "ለበረከት ትረፊ ያላት ነፍስ" - ከ15 ዓመት በፊት የተገባ ስዕለት እና የጀርመን ቤተክርስቲያን ፍቅር 💧⛪
* "አምላኬ ሆይ! ካዳንከኝ፣ በየዓመቱ በጥምቀት በዓል ለምዕመናን ውሃ አቀርባለሁ!"
#ethiopia | በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው የጀርመኖች ቤተ ክርስቲያን፤ በየዓመቱ በጥምቀት በዓል ለሚያልፉ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ውሃ ሲያድል ማየት የተለመደ ነው። ይህ በጎ ተግባር ግን ከጀርባው ጥልቅ የሆነ የእምነት እና የፈውስ ታሪክ አለው።
ታሪኩ እንዴት ጀመረ?
የቤተክርስቲያኑ ሰራተኛ የሆነው አቶ እንዳለ ጌታቸው (ጃጓር)፤ ከ15 ዓመታት በፊት ለጥምቀት መንገድ እያስዋበ ሳለ በኤሌክትሪክ አደጋ ክፉኛ ተጎዳ። በሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖም "ካዳንከኝ ውሃ አጠጣለሁ" ሲል ለአምላኩ ተሳለ።
ፈጣሪ ጸሎቱን ሰምቶ አዳነው! አቶ እንዳለ በመጀመሪያው ዓመት በብቸኝነት ጀመረ፤ ቀጥሎ ግን የጀርመን ቤተክርስቲያን ፓስተሮች እና አስተዳዳሪዎች "እኛም ካንተ ጋር ነን" ብለውት እነሆ ለ15 ዓመታት ይህንን የፍቅር ማዕድ አብረው እያቀረቡ ይገኛሉ።
ፓስተር ዮጋን ክላይን እንዳሉት፤ ይህ ተግባር የሃይማኖት ልዩነትን ተሻግሮ የሰው ልጅ ለሰው ያለውን ክብርና ፍቅር የሚገልጽበት ትልቅ ምስክርነት ነው።
ለበረከት ትረፊ ያላት ነፍስ በጃጓር ጉዳት ተነስታ ዛሬ ለሺዎች የፍቅር ውሃ ሆና እየፈሰሰች ነው! ክብር ለፍቅር እና ለአብሮነት! 🙌🇪🇹
(AMN)
#timket #germanchurch #unity #love #humanity #ethiopia #addisababa #inspiration

Comments