7 hours ago
በአሜሪካ ፍሬስኖ ከተማ በተካሄደ ድግስ ላይ በተነሳ አለመግባባት የ26 ዓመቷ ማሪዮን ፀጋይ ህይወት አለፈ
* ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር ውላለች
#ethiopia | በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ፍሬስኖ ከተማ በሚገኝ የመኖሪያ ቤት ድግስ ላይ በተከሰተ የጥይት ተኩስ የ26 ዓመቷ ወጣት ማሪዮን ፀጋይ ህይወቷ ማለፉን የሀገሩ ፖሊስ አስታወቀ።
የፍሬስኖ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባወጣው መረጃ መሰረት ቅዳሜ ምሽት ተኩስ መከተሱን የሚገልፅ ጥሪ ደርሶት ፍሩት እና ሺልድስ በተባሉ መንገዶች አካባቢ ሲደርስ ማሪዮን ፀጋይ በነጠረ ጥይት ተመታ አግኝቷታል።
ተጎጂዋ ወዲያውኑ ወደ ህክምና ማዕከል ተወስዳ የተደረገላት የህይወት አድን እርዳታ ሳይሳካ ቀርቶ ህይወቷ ልታልፍ ችሏል።
የግድያ ወንጀሉን መርማሪዎች ባደረጉት ማጣራት በድግሱ ላይ በማሪዮን ፀጋይ እና በ24 ዓመቷ ኔማዲያ ክናክልስ መካከል በተነሳ የቃላት ጭቅጭቅ እና አለመግባባት ሳቢያ ተኩሱ እንደተከፈተ ለማወቅ ተችሏል።
የግድያ ወንጀሉን ፈፅማለች የተባለችው የ24 ዓመቷ ኔማዲያ ክናክልስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ በነፍስ ግድያ ወንጀል ከተከሰሰች በኋላ በፍሬስኖ ካውንቲ ማሰሪያ ቤት እንድትቆይ ተደርጋለች።
የፍሬስኖ ፖሊስ መምሪያ ስለ ክስተቱ ተጨማሪ መረጃ ያለው ማንኛውም አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
ማሪዮን ፀጋይ በቡላርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙያ ማዕከል ውስጥ በነበራት ንቁ ተሳትፎ እና በፈጠራ የታጀበ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቷ የሚታወስ ስም የነበራት ሲሆን፣ ላበረከተችው አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠትም በማዕከሉ የተማሪዎች መርሃ ግብር በእሷ ስም ተሰይሞላት እንደነበር ይታወቃል።
#marionetsegay #justiceformarione #fresno #california #crimenews #bullardhighschool #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments