1 month ago
የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገቡት አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና አትሌት ፎቴን ተስፋይ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
#ethiopia | በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል በሴቶች ያሸነፈችው አትሌት ፎቴን ተስፋይ አዲስ አበባ ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ርቀቱን 56 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመጨረስ፣ በዩጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ የነበረውን 57 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል አዲሱን የዓለም ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል።
በሴቶች ውድድር ደግሞ አትሌት ፎቴን ተስፋይ 1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በመስበር በአንደኝነት አጠናቃለች።
አትሌቶቹ አዲስ አበባ ሲደርሱ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት የማነ ፀጋይ፣ የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ፣ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ፣ የአትሌቶቹ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በፌዴራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ አጃቢነት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
#ethiopianathletics #yomifkejelcha #foteintesfay #halfmarathon #worldrecord #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments