20 days ago
ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ ራዕይ የህፃናት መርጃን ጎበኙ
#ethiopia | ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት ጎበኙ።
በጉብኝታቸውም ድርጅቱ ልዩ የድጋፍ ፍላጎት ላላቸው ህፃናትና ወጣቶች እየሰጠ ያለውን የሙያ ስልጠና፣ የችሎታ ማሳያና ሌሎች የድጋፍ ሥራዎች ተመልክተዋል።
ዶ/ር ወዳጄነህ በጉብኝቱ ወቅት ህፃናቱ በሽመና፣ በሙዚቃ፣ በሸክላ ሥራና በሥነ ጥበብ ያላቸውን ችሎታ ሲያሳዩ ተመልክተዋል። ከጠበቁት በላይ በመደሰታቸውም፣ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በመተባበር ለመቆም ቃል ገብተዋል።
ዶ/ር ወዳጄነህ እንደገለጹት፣ ልዩ የድጋፍ ፍላጎት ያላቸው ህፃናትና ወጣቶች ተገቢውን ዕድልና ድጋፍ ሲያገኙ ችሎታቸውን ማሳየትና ማዳበር ይችላሉ። በራዕይ የህፃናት መርጃ ያዩት ሥራም ይህንን በግልጽ እንዳሳየ ገልጸዋል።
በተለይም በየቤቱ ተዘግተው የሚኖሩ ብዙ ህፃናትና ወጣቶች የመማር፣ የመሰልጠንና ችሎታቸውን የማሳደግ ዕድል እንዲያገኙ ድርጅቱ ሥራውን ማስፋፋት እንዳለበት ጠቁመዋል። ህፃናቱን ከጥቃት መጠበቅና የሚያገኙትን ዕድል ማስፋትም አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ሰሎሜ ኩምሳ በበኩላቸው፣ ዶ/ር ወዳጄነህ ድርጅቱን መጎብኘታቸው ለህፃናቱና ለሚሠሩት ሥራ ትልቅ ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ሰሎሜ ገለጻ፣ ራዕይ የህፃናት መርጃ በአሁኑ ወቅት የአእምሮ እድገት ውስንነትና የመማር ችግር ያላቸውን ወጣቶች በሙያ ስልጠና፣ በመሠረታዊ የኮምፒዩተር ትምህርት፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በስፖርትና በሌሎች ዘርፎች እያሰለጠነ ይገኛል። በተጨማሪም ለህፃናቱ የሥነ ልቦና፣ የሕክምናና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን ይሰጣል።
ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ከ350 በላይ ወጣቶችን ደግፏል። በአዲስ አበባ በአምስት ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ወደ ሰባት ትምህርት ቤቶች ሥራውን ሲያከናውን፣ በአዳማም በአንድ ትምህርት ቤት ሥራ ጀምሯል።
ከሚሰጡት የሙያ ስልጠናዎች መካከል ሽመና ዋነኛው ሲሆን፣ ከሰለጠኑ ወጣቶች መካከል 12 ወጣቶች የሽመና ባለሙያዎች ሆነው ነጠላ፣ ሻርፕና የባህል ልብሶችን እያመረቱ መሆኑን ወይዘሮ ሰሎሜ አስረድተዋል።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት ወላጆችና መምህራን ስለህፃናቱ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙም ስልጠና ይሰጣል። በተለይም ልዩ የድጋፍ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ከጥቃት እንዲጠበቁና በማህበረሰቡ ዘንድ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርቧል።
ድርጅቱ በኢትዮጵያ በዶ/ር ፅጌ ጥበቡ መሥራችነት የተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ የአእምሮ እድገት ውስንነትና ሌሎች የአካል ጉዳቶች ያሉባቸውን ህፃናትና ወጣቶች በመንፈሳዊ፣ በስሜታዊ፣ በትምህርታዊና በሙያዊ ፕሮግራሞች በመደገፍ በክብርና በነፃነት እንዲማሩ፣ እንዲሰሩና እንዲኖሩ የሚያስችል አካባቢ ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።
በተጨማሪም ወጣቶችን በሸማ ሙያ፣ በኮምፒዩተርና በኮዲንግ፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ሥዕልና በስፖርት በማሰልጠን ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና በራሳቸው አቅም ለመስራት የሚያስችላቸውን ዕድል ለመፍጠር እየሰራ ነው።
#ethiopia #visionchildrensupportorganization #drwodajeneh #empoweringyouth #communitysupport #inclusion #visionchildrensupport #drwodajeneh #disabilitysupport #inclusion #communityservice #ethiopiannews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
አምባሳደር ስለሺ ኡመር የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲና የወጣቶች አመራር የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው
#ethiopia | የሴፍ ላይት ኢኒሼቲቭስ (Safe Light Initiatives) መስራችና ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ስለሺ ኡመር፣ በ«ግሎባል ኤክሰለንስ ኤንድ ሊደርሺፕ አዋርድስ አፍሪካ 2026» (Global Excellence & Leadership Awards Africa 2026) ላይ የ«ቪዥነሪ ሊደር ኢን ግሎባል ዲፕሎማሲ ኤንድ ዩዝ ሊደርሺፕ» (Visionary Leader in Global Diplomacy and Youth Leadership Award) ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።
በኢንሳይት ሰክሰስ (Insight Success) አዘጋጅነትና በኢንሳይት ኤክሰለንስ አዋርድስ (Insight Excellence Awards) አጋርነት የተበረከተው ይህ ታዋቂ ሽልማት፣ አምባሳደር ስለሺ ወጣቶችን በማብቃት፣ የአመራር ብቃትን በማሳደግ እና ትርጉም ያለው ማህበራዊ ለውጥ በማምጣት ረገድ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተሰጠ እውቅና ነው።
ይህ ታላቅ ስኬት በቀጣይነትም ለቀጣዩ ትውልድ መነሳሳትን በመፍጠር ማህበረሰባዊ እድገትን እንደሚያፋጥን ታምኖበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#safelightinitiatives #globalexcellenceawards2026 #youthleadership #globaldiplomacy #visionaryleader #empoweringyouth #africaleaders

Comments