30 days ago
ሮቦት ውሻዎ ሊሰሚሩ ነው
#ethiopia | የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ከስካይቦርን (Skyborne) ኩባንያ ጋር በ6.5 ሚሊዮን ዶላር የተፈራረመው ስምምነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታጠቁ የሮቦት ውሾችን ወደ ጦር ግንባር በይፋ ሊቀላቅል መሆኑ ተሰምቷል።
ኮዲያክ (CODiAQ) የተሰኘውና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀው ይህ ሮቦት፣ በተለይ ወታደሮች ከፍተኛ የሕይወት መስዋዕትነት ሊከፍሉባቸው በሚችሉ አስቸጋሪ የፊት መስመር ግዳጆች ላይ እንዲሰማራ ተደርጎ የተሰራ ነው።
ሮቦቱ ጠላትን ከመሰለል ባለፈ ህንፃዎችን ዘልቆ በመግባት ጥቃት የመፈጸም፣ ፈንጂዎችን የመለየትና በጠባብ ስርጦች ውስጥ የሚደረጉ ውጊያዎችን በብቃት የመወጣት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ጥብቅ የታክቲክ ግምገማ እየተደረገለት የሚገኘው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ውጤታማነቱ ሲረጋገጥ በአሜሪካ ልዩ ኮማንዶ ኃይሎች ውስጥ በቋሚነት ግዳጅ ላይ የሚሰማራ ሲሆን፤ ይህም የወደፊቱ የጦርነት ስልት ከሰው ኃይል ይልቅ በቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ጥገኛ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#technology #militaryrobot #ai #skyborne #codiaq #futurewarfare #innovation #defensenews

5 months ago
🚀 F-16 Fighting Falcon፡ የሰማይ ላይ ንጉስ እና የጦር ሜዳዎች ፈርጥ!
በዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች ታሪክ ውስጥ እንደ F-16 ስሙ የገነነ እና በአለም ዙሪያ ተመራጭ የሆነ ጀት የለም። ይህ አውሮፕላን ለምን የብዙ ሀገራት አየር ኃይል የጀርባ አጥንት ሊሆን ቻለ?
🔹 የF-16 አመጣጥ እና ስሪት
F-16 በመጀመሪያ የተሰራው በአሜሪካው ሎክሂድ ማርቲን (Lockheed Martin) ኩባንያ ነው። መጀመሪያ ላይ ለቀላል የአየር ላይ ውጊያ (Dogfighting) ታስቦ የተሰራ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ለማንኛውም ዓይነት ተልዕኮ (Multi-role) የሚበቃ ብቃት ያለው ድንቅ ጀት ሆኗል።
🔹 የማጥቃት ብቃቱ (Combat Capability)
F-16 ሁለገብ የሚባለው ያለምክንያት አይደለም እነዚህን ገዳይ ችሎታዎች የታጠቀ ነው፡
* የአየር ላይ ውጊያ (Air-to-Air): እጅግ ዘመናዊ የሆኑ እንደ AIM-120 AMRAAM ያሉ ሚሳኤሎችን በመጠቀም የጠላት ጀትን ሳያዩት ከሩቅ የመምታት አቅም አለው።
* የምድር ጥቃት (Air-to-Ground): በሌዘር የሚመሩ ቦምቦችን እና ሚሳኤሎችን በመሸከም የጠላትን ምሽግ፣ ታንክ እና ራዳር በከፍተኛ ትክክለኛነት ያወድማል።
* ኤሌክትሮኒክ ውጊያ: የጠላትን ራዳር የማታለል እና የመርበሽ (Jamming) የቴክኖሎጂ የበላይነት አለው።
🔹 ልዩ የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ብቃቶች
* ፍጥነት እና ቁመት፦ ከድምፅ ፍጥነት ሁለት እጥፍ በላይ (Mach 2.0) መብረር ይችላል። እስከ 50,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሆኖ የመዋጋት አቅም አለው።
* ተለዋዋጭነት (Maneuverability): በጠባብ ቅፅበት ውስጥ የመታጠፍ እና የመገልበጥ ብቃቱ ተወዳዳሪ የለውም። ይህ ለቅርብ ርቀት ውጊያ እጅግ አስፈላጊ ነው።
* የአብራሪው እይታ፦ የF-16 የመስታወት ክዳን (Canopy) 360 ዲግሪ እይታን ለአብራሪው ይሰጣል። ይህም በውጊያ ወቅት ጠላትን ለመቆጣጠር ይረዳል።
🔹 ለምን አሁንም ተፈላጊ ሆነ?
ምንም እንኳን አዳዲስ እንደ F-35 ያሉ ጀቶች ቢመጡም፣ F-16 አሁንም ተመራጭ የሆነው ለአጠቃቀም ቀላል በመሆኑ፣ የጥገና ወጪው ዝቅተኛ በመሆኑ እና በማንኛውም የአየር ሁኔታ ውስጥ መሥራት ስለሚችል ነው።
ኢትዮጵያ ይህንን የጦር ጀት ካልታጠቀች ብትታጠቅ ምን ይመስላችኃል?
ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇 #f16 #airforce #militarytech #aviationnews #ethiopia #defensenews

Comments